إعدادات العرض
ተመለስና ደግመህ ስገድ! አንተ አልሰገድክም።
ተመለስና ደግመህ ስገድ! አንተ አልሰገድክም።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) መስጂድ ገቡ። አንድ ሰውዬም መስጂድ ገባና ሰገደ። ነቢዩንም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሰላምታ አቀረበላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱና እንዲህ አሉት "ተመለስና ደግመህ ስገድ! አንተ አልሰገድክም።" ቀደም ብሎ እንደሰገደው ለመስገድ ተመለሰ። ቀጥሎም በመምጣት ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሰላምታ አቀረበላቸው። እርሳቸውም "ተመለስና ደግመህ ስገድ! አንተ አልሰገድክም።" እያሉት ሶስት ጊዜ ተመላለሰ። እርሱም "ያ በእውነት በላኮት ጌታ እምላለሁ! ከዚህ ውጪ አሳምሬ መስገድ አልችልምና አስተምሩኝ።" አላቸው። እርሳቸውም "ወደ ሶላት የቆምክ ጊዜ ተክቢራ አድርግ፤ ከዚያም ከቁርአን (ፋቲሓንና) የገራልህን ቅራ! ከዚያም በተረጋጋ ሁኔታ አጎንብስ፤ ከዚያም ቀጥብለህ በቆምክበት እስክትረጋጋ ድረስ ተነሳ፤ ከዚያም በሱጁድህ እስክትረጋጋ ድረስ ሱጁድ አድርግ፤ ከዚያም ተረጋግተህ እስክትቀመጥ ድረስ ተነሳ! በሁሉም የሶላትህ ክፍልም ይህንን ፈፅም።" አሉት።»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî Русский Tiếng Việt অসমীয়া Kiswahili Nederlands ગુજરાતી සිංහල ไทยالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) መስጂድ ገቡ። ከርሳቸው በኋላም አንድ ሰውዬ በመግባት በፍጥነት ሁለት ረከዓ ሰገደ። ይሁን እንጂ ሲቆምም፣ ሲያጎነብስም፣ ሱጁድ ሲወርድም እርጋታን አልተላበሰም ነበር። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሶላቱን ይከታተሉት ነበር። ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመስጂዱ አንድ ጎን ስር ተቀምጠው ሳለ ወደርሳቸው በመምጣት ሰላምታ አቀረበላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን ከመለሱለት በኋላ እንዲህ አሉት: አንተ አልሰገድክምና ተመለስና ሶላትህን ደግመህ ስገድ። ተመልሶም ቀደም ብሎ እንደሰገደው በፍጥነት ሰገደና ድጋሚ መጥቶ ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሰላምታን አቀረበ። እርሳቸውም እንዲህ አሉት: አንተ አልሰገድክምና ተመልሰህ ስገድ። ይህንንም ሶስት ጊዜ ፈፀመ። ሰውዬውም "በእውነት በላኮት ጌታ እምላለሁ! ከዚህ ውጪ አሳምሬ መስገድ አልችልምና አስተምሩኝ።" አለ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉት: "ወደ ሶላት የቆምክ ጊዜ የመክፈቻ ተክቢራ አድርግ፤ ከዚያም የቁርአን እናትን (ፋቲሓን)ና አላህ እንድትቀራ የሻልህን ቅራ፤ ከዚያም ባጎነበስክበት ሁኔታህ ላይ ሆነህ እስክትረጋጋ ድረስ አጎንብስ። ይህም መዳፎችህን ጉልበቶችህ ላይ በማድረግና ወገብህን በመዘርጋት ለሩኩዕህ በመመቻቸት ነው።፣ ከዚያም ቀና በል፤ አጥንቶችህ ወደ መገጣጠሚያቸው እስኪመለሱና ቆመህ እስክትስተካከል ድረስ ጀርባህን ቀጥ አድርግ፤ ከዚያም ሱጁድ ላይ ባለህበት ሁኔታ እስክትረጋጋ ድረስ ሱጁድ ውረድ። ይህም ግንባርን ከአፍንጫ ጋር፣ ሁለት እጆችን፣ ሁለቱ ጉልበቶችንና የሁለት እግሮች ጣቶችን ጫፍ መሬት ላይ በማመቻቸት በግንባር መደፋት ነው። ከዚያም በሁለቱ ሱጁዶች መካከል ተረጋግተህ እስክትቀመጥ ድረስ ከሱጁድህ መነሳት ነው። ከዚያም በሶላትህ በሁሉም ረከዓዎች ውስጥ ይህንን ፈፅም።"فوائد الحديث
እነዚህ የሶላት ማዕዘኖች ናቸው። በመርሳትም ይሁን ባለማወቅ መተው አይቻልም። የዚህም ማስረጃው ነቢዩ ሰጋጁን ማስደገማቸው ነው። ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እርሱን በማስተማር ብቻ አልተብቃቁም። ይልቁንም እንዲደግመው አዘዙት።
ሶላት ውስጥ መረጋጋት ከሶላት ማእዘናት መካከል አንዱ ነው።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ከሶላት ግዴታዎች መካከል አንዱን ያጓደለ ሶላቱ እንደማይበቃ ያስረዳናል።"
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ለተማሪና አላዋቂ ሰው ማዘንና ለስላሳ መሆን እንደሚገባ፤ ጉዳዩን ለርሱ ግልፅ ማድረግና የተፈለገበትን አላማ ብቻ ማሳጠር እንደሚገባ፤ በርሱ ደረጃ ያሉ ሰዎች ሊሸመድደውና ሊተገብረው የማይችላቸውን ግን-ደግሞ ማሟያ የሆኑ ዕውቀቶችን ትቶ ወሳኝ የሆኑ ነገሮችን ብቻ በማስተማር መቆጠብ እንደሚገባም ያስረዳናል።"
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ሙፍቲ አንድ ነገር ሲጠየቅ ጠያቂው ከጠየቀው ውጪ ሊነገረው የሚያስፈልገው ሌላ ነገር ካለ ባይጠይቀው እንኳ ለርሱ መዘርዘር እንደሚወደድ ያስረዳናል። ይህም የማይጠቅምን ከመናገር መካከል የሚመደብ ሳይሆን ከመመካከር የሚመደብ ነው።"
"ከዚህ ውጪ አሳምሬ መስገድ አልችልምና አስተምሩኝ።" ከሚለው ንግግር ጉድለትን ማመን ያለውን ደረጃ እንረዳለን።
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ከዚህ ሐዲሥ በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል ያለውን ደረጃ፤ ተማሪ ዐሊም እንዲያስተምረው መጠየቅ እንደሚገባው እንረዳለን።"
በመገናኘት ወቅት ሰላምታ መለዋወጥ እንደሚወደድ፤ ሰላምታ መመለስ ግዴታ መሆኑን፤ በአጭር ወቅት እንኳ ቢሆን በተደጋጋሚ ከተገናኙ ሰላምታን መደጋገሙ እንደሚወደድና ሁሉንም የሚቀርቡለት ሰላምታዎች መመለስ ግዴታ እንደሆነ እንረዳለን።
التصنيفات
የሶላት አሰጋገድ