إعدادات العرض
እናታችን ዓኢሻን እንዲህ ብየ ጠየቅኳት: "ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ቤታቸው የገቡ ጊዜ በምን ነበር የሚጀምሩት?" እርሷም "በመፋቅ"…
እናታችን ዓኢሻን እንዲህ ብየ ጠየቅኳት: "ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ቤታቸው የገቡ ጊዜ በምን ነበር የሚጀምሩት?" እርሷም "በመፋቅ" በማለት መለሰችልኝ።
ከሹረይሕ ቢን ሃኒእ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «እናታችን ዓኢሻን እንዲህ ብየ ጠየቅኳት: "ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ቤታቸው የገቡ ጊዜ በምን ነበር የሚጀምሩት?" እርሷም "በመፋቅ" በማለት መለሰችልኝ።»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी සිංහල Hausa Kurdî Kiswahili Português Nederlands Tiếng Việt অসমীয়া ગુજરાતી پښتو ไทย മലയാളം नेपालीالشرح
ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መመሪያ መካከል በማንኛውም ወቅት በምሽትም ሆነ በቀን ቤታቸው የገቡ ጊዜ በመፋቂያ መጀመር አንዱ ነበር።فوائد الحديث
በሁሉም ወቅት ባጠቃላይ መፋቂያ መደንገጉን እንረዳለን። ነቢዩ ይወደዳል ባሉበት ወቅት ደሞ ይበልጥ አፅንዖት ይሰጠዋል። ከነርሱም መካከል: ቤት በሚገባ ወቅት፣ ለሶላት በሚቆም ወቅት፣ ዉዱእ በሚደረግበት ወቅት፣ ከእንቅልፍ ከነቁ በኋላና የአፍ ጠረን በሚለወጥበት ወቅት ነው።
ታቢዒዮች እርሳቸውን ለመከተል ብለው ስለነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሁኔታዎችና ሱናዎች በመጠየቅ ላይ የነበራቸው ጥረት እንረዳለን።
እናታችን ዓኢሻ (ረዺየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ቤት በሚገቡ ወቅት ስለነበራቸው ሁኔታ መጠየቋ እውቀትን ከባለቤቱና በጉዳዩ እጅግ አዋቂ ከሆነው መውሰድ እንደሚገባ እንረዳለን።
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ቤት በሚገቡ ወቅት አፋቸውን ማፅዳታቸው ሚስቶቻቸውን በመልካም መኗኗራቸውን ያስረዳናል።
التصنيفات
ተፈጥሯዊ ሱናዎች