የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሌላ ጊዜያት ለአምልኮ ከሚጥሩት የተለየ በመጨረሻዎቹ አስሩ የረመዷን ቀናት ይጥሩ ነበር።

የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሌላ ጊዜያት ለአምልኮ ከሚጥሩት የተለየ በመጨረሻዎቹ አስሩ የረመዷን ቀናት ይጥሩ ነበር።

የአማኞች እናት ከሆነችው ከዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው፦ "የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሌላ ጊዜያት ለአምልኮ ከሚጥሩት የተለየ በመጨረሻዎቹ አስሩ የረመዷን ቀናት ይጥሩ ነበር።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የመጨረሻዎቹ አስሩ የረመዷን ቀናት የመጡ ጊዜ በአምልኮና ትርፍ ስራዎች ላይ ጥረት ያደርጉ ነበር። በሌላ ወቅት ይጥሩ ከነበሩት የበለጠ በመልካም ስራ አይነቶች፣ በአምልኮና፣ በበጎ አድራጎት ዘርፎች አበዝተው ይጥሩ ነበር። ይህም እንዚህ ሌሊቶች ያላቸው ደረጃ የላቀና ከፍያለ ስለሆነ እንዲሁም ለይለተል ቀደርንም ለመፈለግ ነው።

فوائد الحديث

በረመዷን ወር ባጠቃላይ በተለይ የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ላይ መልካም ስራዎችንና የተለያዩ አምልኮዎችን በማብዛት መነሳሳቱን እንረዳለን።

የመጨረሻዎቹ አስር የረመዷን ቀናት ከሀያ አንደኛው ምሽት ጀምሮ እስከ ወሩ መጨረሻ ድረስ ይሄዳል።

የላቁ ወቅቶችን በአምልኮ ማሳለፍ እንደሚወደድ እንረዳለን።

التصنيفات

የረመዿን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት