إعدادات العرض
አንዳችሁ በአላህ ላይ ያለውን እሳቤ ሳያሳምር እንዳይሞት።
አንዳችሁ በአላህ ላይ ያለውን እሳቤ ሳያሳምር እንዳይሞት።
ከጃቢር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከመሞታቸው ሶስት ቀናት በፊት እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ "አንዳችሁ በአላህ ላይ ያለውን እሳቤ ሳያሳምር እንዳይሞት።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt සිංහල Hausa Kurdî Kiswahili Português தமிழ் Nederlands অসমীয়া ગુજરાતી پښتو ไทย മലയാളം नेपालीالشرح
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ሙስሊም በአላህ ላይ ያለውን እሳቤ አሳምሮ ካልሆነ በቀር እንዳይሞት አነሳሱ። ይህም ጣእረ ሞት ላይ የሆነ ጊዜ አላህ እንደሚያዝንለትና ይቅር እንደሚለው በማሰብ ተስፈኝነቱን በማመዘን ነው። በሸሪዓ አላህን መፍራት የተፈለገው ስራችንን እንድናሳምር ስለሚረዳን ነው። ይህ ያለበት ሁኔታ ደግሞ የስራ ሁኔታ አይደለምና በዚህ ሁኔታ ላይ የሚፈለገው ተስፈኝነትን ማመዘን ነው።فوائد الحديث
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ኡመታቸውን በማቅናት (በማመላከት) ላይ ያላቸውን ጥረትና በሁሉም ሁኔታቸው ላይ ለኡመታቸው ያላቸውን ከፍተኛ እዝነት እንረዳለን። በሞቱበት በሽታ ላይ ሆነው እንኳ ኡመታቸውን ይመክራሉም የመዳን መንገድንም ይጠቁማሉ።
ጢቢይ እንዲህ ብለዋል: "በምትሞቱ ወቅት በአላህ ላይ የሚኖራችሁ እሳቤ ያማረ እንዲሆን ዛሬ ላይ ስራችሁን አሳምሩ። ከመሞቱ በፊት ስራውን ያበላሸ ሰው በሚሞትበት ወቅትም እሳቤው ይበላሻልና።"
ለአንድ ባሪያ የተሟላ የሚባለው ፍርሃቱና ተስፋው ተመጣጣኝ ሆነው ውዴታው ሲያመዝን ነው። ውዴታ መርከቧ ናት፤ ተስፋ ቀዛፊው ነው፣ ፍርሃት ሹፌሩ ነው። አላህ ደግሞ በችሮታውና በጸጋው አድራሹ ነው።
ጣዕረ ሞት ላይ ወደሆነ ሰው የቀረበ ሰው ጣዕረ ሞት ላይ ላለው ሰው ተስፈኝነትንና በአላህ ያለውን እሳቤ ማሳመርን እንዲያመዝን ማድረግ ይገባዋል። እዚህ ሐዲሥ ውስጥም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህን የተናገሩት ከመሞታቸው ሶስት ቀን በፊት እንደሆነ ተዘግቧል።
التصنيفات
የቀልብ ተግባራት