إعدادات العرض
ወንድምህ በዳይም ሆነ ወይም ተበዳይ እርዳው።
ወንድምህ በዳይም ሆነ ወይም ተበዳይ እርዳው።
አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዳስተላለፉት እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦ "ወንድምህ በዳይም ሆነ ወይም ተበዳይ እርዳው።" አንድ ሰውዬም እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ተበዳይ የሆነ ጊዜ እረዳዋለሁ። እስኪ ንገሩኝ በዳይ በሆነ ጊዜ እንዴት ነው የምረዳው?" እርሳቸውም "ከመበደል ታቅበዋለህ ወይም ትከለክለዋለህ። ይህ እርሱን መርዳት ነው።" ብለው መለሱ።»
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Tiếng Việt Magyar ქართული Kiswahili සිංහල Română অসমীয়া ไทย Português मराठी دری ភាសាខ្មែរالشرح
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሙስሊም ወንድም በዳይም ሆነ ወይም ተበዳይ እንዲረዳ አዘዙ። አንድ ሰውዬም እንዲህ አለ: የአላህ መልክተኛ ሆይ! ተበዳይ በሆነ ጊዜ በደልን ከርሱ ላይ በማስወገድ እረዳዋለሁ። ንገሩኝ እስኪ በዳይ ከሆነ እንዴት ነው የምረዳው? እርሳቸውም እንዲህ በማለት መለሱ: ከበደል ትከለክለዋለህ፣ እጁን ትይዘዋለህ፣ ትገታዋለህ፣ ታቅበዋለህ። ይህ በሰይጣኑና በመጥፎ በምታዘው ነፍሱ ላይ እያገዝከው ነው።فوائد الحديث
በሙስሊሞች መካከል የእምነታዊ ወንድማማችነት ሀቆች መካከል አንዱን ሀቅ ተገንዝበናል።
የበዳይን እጅ መያዝና ከበደል መከልከል እንደሚገባ እንረዳለን።
ተበዳዮች ሁነውም ይሁን በዳይ ሁነው እርስ በርስ ይረዳዱ የነበሩትን የድንቁርና አስተሳሰብ እስልምና ተፃሮ መምጣቱን እንረዳለን።
التصنيفات
ሙስሊም ማህበረሰብ