إعدادات العرض
አቡ ዘር ሆይ! መረቅ የቀቀልክ ጊዜ ውሃውን አብዛ! ጎረቤቶችህንም ተከታተል።
አቡ ዘር ሆይ! መረቅ የቀቀልክ ጊዜ ውሃውን አብዛ! ጎረቤቶችህንም ተከታተል።
ከአቡ ዘር ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል: "አቡ ዘር ሆይ! መረቅ የቀቀልክ ጊዜ ውሃውን አብዛ! ጎረቤቶችህንም ተከታተል።"»
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Tiếng Việt Nederlands Kiswahili অসমীয়া ગુજરાતી සිංහල Magyar ქართული Română ไทย Português मराठी ភាសាខ្មែរ دریالشرح
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አቡ ዘር አልጚፋሪይን ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - መረቅ የቀቀለ ጊዜ ውሃውንና መረቁን እንዲያበዛና ከመረቁ ለጎረቤቶቹ በመላክም እንዲከታተላቸው አነሳሱት።فوائد الحديث
ከጎረቤት ጋር መልካም በሆነ መልኩ በመኗኗር ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
በጎረቤቶች መካከል ስጦታ መሰጣጠታቸው እንደሚወደድ እንረዳለን። ይህም ውዴታን ስለሚያመጣና ቅርርብን ስለሚጨምር ነው። ምግቡ የሚጣራ መአዛ ካለውና ጎረቤቶቹም እንደሚያስፈልጋቸው ከታወቀ ደግሞ ይህን ስጦታ መስጠት አፅንዖት የተሰጠው ጉዳይ ይሆናል።
ብታንስ እንኳ የገራልንን ጥሩን ነገር በመለገስ ላይና ለሙስሊሞች ደስታ ምክንያት በመሆን ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
التصنيفات
ስምምነትና የጉርብትና ህግጋት