إعدادات العرض
ሚስቱን በመቀመጫዋ የተገናኛት ሰው የተረገመ ነው።
ሚስቱን በመቀመጫዋ የተገናኛት ሰው የተረገመ ነው።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ሚስቱን በመቀመጫዋ የተገናኛት ሰው የተረገመ ነው።"»
[ሐሰን ነው።] [አቡዳውድ፣ ነሳኢ በኩብራ ውስጥ፣ አሕመድ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية Bosanski English فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو हिन्दी 中文 ئۇيغۇرچە Kurdî Português Nederlands অসমীয়া Tiếng Việt ગુજરાતી Kiswahili پښتو සිංහල Hausa ไทยالشرح
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ባል ሚስቱን በመቀመጫዋ በኩል መገናኘቱን ከለከሉ። ከአላህ እዝነት የተባረረና የተረገመ መሆኑንም ገለፁ። ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል የሚመደብም ነው።فوائد الحديث
ሴቶችን በመቀመጫቸው በኩል መገናኘት ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
ሚስትን ከመቀመጫዋ ውጪ ባለ አካሏ መጠቀም ይፈቀዳል።
ሙስሊም የሆነ ሰው አላህ እንዳዘዘው ሚስቱን በብልቷ በኩል መገናኘት ነው ያለበት። በመቀመጫ በኩል መገናኘት ግን ተፈጥሮን መፃረር (ማበላሸት)፣ ዘርን ማባከን፣ ንፁህ ተፈጥሮ ያለበትን መፃረር፣ በጥንዶቹ ላይም ከመጠን ያለፈ ጉዳት የሚያደርስ ነው።
التصنيفات
የጋብቻ ስነ ስርዓት