إعدادات العرض
ሴቶች ጋር ከመግባት ተጠንቀቁ!" አንድ ከአንሷር የሆነ ሰውዬም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ስለባል ቅርብ ዘመዶች ንገሩኝ እስኪ?" አለ። እርሳቸውም "የባል ቅርብ ዘመድማ ሞት ነው።" አሉ።
ሴቶች ጋር ከመግባት ተጠንቀቁ!" አንድ ከአንሷር የሆነ ሰውዬም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ስለባል ቅርብ ዘመዶች ንገሩኝ እስኪ?" አለ። እርሳቸውም "የባል ቅርብ ዘመድማ ሞት ነው።" አሉ።
ከዑቅበህ ቢን ዓሚር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ሴቶች ጋር ከመግባት ተጠንቀቁ!" አንድ ከአንሷር የሆነ ሰውዬም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ስለባል ቅርብ ዘመዶች ንገሩኝ እስኪ?" አለ። እርሳቸውም "የባል ቅርብ ዘመድማ ሞት ነው።" አሉ።
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी සිංහල ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî Русский Nederlands অসমীয়া Tiếng Việt Kiswahili ગુજરાતી پښتو ไทย Oromoo Românăالشرح
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከእንግዳ ሴቶች ጋር ከመቀላቀል እንዲህ በማለት አስጠነቀቁ "በሴቶች ላይ ከመግባትና ሴቶችም እናንተ ዘንድ እንዳይገቡ ነፍሳችሁን ጠብቁ!" አንድ የአንሷር ሰውዬም እንዲህ አለ: እስኪ ንገሩኝ የባል ወንድም፣ የወንድሙ ልጅ፣ አጎቱ፣ የአጎቱ ልጅ፣ የእህቱ ልጅና የመሳሰሉት ባታገባ ኖሮ ልታገባቸው የሚፈቀዱላት የባል ቅርብ ዘመዶች ቢገቡስ ይፈቀዳልን? ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና "ሞትን እንደምትጠነቀቁት እርሱንም ተጠንቀቁት! ከባል ዘመዶች ጋር ገለል ብሎ ማሳለፍ ለሃይማኖት ፈተናና ጥፋት የሚመራ ነው። ከአባቱና ከልጆቹ ውጪ ያሉ የባል ቅርብ ዘመዶችን መከልከል ከሌላው ባዳ ወንድ የበለጠ የተገባ ነው። ይህም ከሌላ ባዳ ጋር ለብቻ ከምታሳልፍበት ጊዜ ይልቅ ከባል ቅርብ ዘመድ ጋር ለብቻ የማሳለፍ እድሉ የበዛ ስለሆነ ከሌላው በበለጠ ከርሱ ጋር መጥፎ ነገር መከሰቱ ስለሚገመትና ያለምንም አውጋዥ ወደ ሴቷ መድረስና ከርሷ ጋር ለብቻ ማሳለፍ ስለሚችል ፈተና የመከሰት እድሉም የሚመች ነው። በተለምዶ የባል ወንድም የወንድሙ ሚስት ብቻዋን እያለች መግባት ቸል የሚባል ጉዳይ ስለሆነ ፈተና መከሰቱ የማይቀር ጉዳይ ነው። ከባዳ ወንድ ጋር ለብቻ ማሳለፍማ የሚጠነቀቁት ጉዳይ ነው። ከርሱ በተቃራኒ ከባል ዘመድ ጋር ለብቻ የማሳለፍ አፀያፊነትና የሚያስከትለው ችግር ግን ከሞት ጋር ይመሳሰላል።فوائد الحديث
ዝሙት ላይ የመውደቂያን መዳረሻ ለመዝጋት ወደ ባዳ ሴቶች ከመግባትና ከነርሱ ጋር ለብቻ ከማሳለፍ መከልከሉን እንረዳለን።
ይህ ክልከላ የሴቷ ቅርብ ዘመዶች ያልሆኑን የባል ወንድምንና ቅርብ ዘመዶቹን ጨምሮ ባዳ ወንዶችን ባጠቃላይ የሚጠቀልል ነው። (ባል በሌለበት) መግባቱ ብቻ ከርሷ ጋር መገለልን ማስፈረዱ የማይቀር ጉዳይ ነው።
መጥፎ ነገር ላይ መውደቅን በመፍራት ብዙሃን ስህተት ላይ የሚወድቁበትን ስፍራ መራቅ ይገባል።
ነወዊ እንዲህ ብለዋል: «የቋንቋ ምሁራን ባጠቃላይ እንደተስማሙት "አሕማእ" ማለት የባል ቅርብ ዘመዶች ናቸው። አባቱ፣ አጎቱ፣ ወንድሙ፣ የወንድሙ ልጅ፣ የአጎቱ ልጅና የመሳሰሉት ማለት ነው። "አኽታን" ማለት ደግሞ የሚስት ቅርብ ዘመዶች ናቸው። "አስሃር" የሚለው ቃል ደግሞ ለሁለቱም የሚውል ስም ነው።»
የባል ዘመድ ከሞት ጋር አመሳስለው የመግለፃቸው ምስጢር:- ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: «ዐረቦች የሚጠሉትን ነገር በሞት ይመስሉታል። የመመሳሰሉም መልክ ከባል ዘመድ ጋር ወንጀል ከተፈፀመ በዲን በኩል እንደሞት ነው፤ ወንጀል ከተፈፀመም ከባል ዘመድ ጋር ተገልላ ያሳለፈችው የመወገር ግዴታ ስላለባት ትሞታለች፤ ባል ቅናቱ ለፍቺ ከገፋፋውም ከባሏ መለየቷ ለሴቷ ጥፋት ነው።»
التصنيفات
የሴቶች ህግጋት