إعدادات العرض
‹ብር በወርቅ እጅ በእጅ ካልሆነ በቀር አራጣ ነው፤ ስንዴ በስንዴ መለዋወጥ እጅ በእጅ ካልሆነ በቀር አራጣ ነው፤ ገብስ በገብስ መለዋወጥ እጅ በእጅ ካልሆነ በቀር አራጣ ነው፤ ተምር…
‹ብር በወርቅ እጅ በእጅ ካልሆነ በቀር አራጣ ነው፤ ስንዴ በስንዴ መለዋወጥ እጅ በእጅ ካልሆነ በቀር አራጣ ነው፤ ገብስ በገብስ መለዋወጥ እጅ በእጅ ካልሆነ በቀር አራጣ ነው፤ ተምር በተምር መለዋወጥ እጅ በእጅ ካልሆነ በቀር አራጣ ነው።›
ከማሊክ ቢን አውስ ቢን ሐደሣን እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ዲርሃም የሚመነዝርልኝ እያልኩኝ ተዘዋወርኩኝ። ጦልሓ ቢን ዑበይዲላህ ከዑመር ቢን ኸጧብ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ዘንድ እያለ እንዲህ አለኝ: "ወርቅህን አሳየንና ከዚያም ተመልሰህ ና! አገልጋያችን የመጣ ጊዜ ገንዘብህን እንሰጥሃለን።" በዚህ ጊዜ ዑመር ቢን ኸጧብ እንዲህ አለ: "በፍፁም! በአላህ እምላለሁ! ወይ አሁን ብሩን ትሰጠዋለህ ወይም ወርቁን ትመልስለታለህ! የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: ‹ብር በወርቅ እጅ በእጅ ካልሆነ በቀር አራጣ ነው፤ ስንዴ በስንዴ መለዋወጥ እጅ በእጅ ካልሆነ በቀር አራጣ ነው፤ ገብስ በገብስ መለዋወጥ እጅ በእጅ ካልሆነ በቀር አራጣ ነው፤ ተምር በተምር መለዋወጥ እጅ በእጅ ካልሆነ በቀር አራጣ ነው።›"»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी සිංහල ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî Nederlands অসমীয়া Tiếng Việt Kiswahili ગુજરાતી پښتو ไทย Oromoo Română മലയാളംالشرح
ታቢዒዩ ማሊክ ቢን አውስ እርሱ ዘንድ በብር ዲርሃም ሊመነዝራቸው የፈለጋቸው የወርቅ ዲናሮች እንደነበሩት ተናገረ። ጦልሓ ቢን ዑበይዲላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ለርሱ "ዲናርህን አምጣና እንየው።" አለ። ቀጥሎ አይቶ ለመግዛት ከወሰነ በኋላ "የብሩን ዲርሃም እንድንሰጥህ በኋላ አገልጋያችን ከመጣ በኋላ ና።" አለው። ዑመር ቢን አልኸጧብ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ቦታው ላይ ነበሩና የዚህን አይነት ግብይይት አወገዙ። ለጦልሓም ብሩን አሁኑኑ እንዲሰጥ አልያም የወሰደውን ወርቅ እንዲመልስ ምሎ ነገረው። የዚህም ምክንያት የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ብር በወርቅ መለዋወጥ ወይም በተገላቢጦሹ መለዋወጥ ተለዋዋጩ በቀጥታ መቀባበል እንዳለበት ያለበለዚያ ግን ይህ ግብይት የተከለከለው አራጣዊና ትክክል ያልሆነ ግብይት እንደሚሆን ማውሳታቸውን ስለዚህም ወርቅ በብር ብር በወርቅ እጅ በእጅ ካልሆነና የተሟላ የሆነ ቅብብል ከሌለ በቀር መገበያየት እንደማይፈቀድ፤ ልክ እንደዚሁ ስንዴ በስንዴ፣ ገብስ በገብስ፣ ተምር በተምር መለዋወጥ አምሳያውን በአምሳያው፣ ኪሎ በኪሎ፣ ስፍር በስፍር፣ እጅ በእጅ ካልሆነ በቀር መገበያየት እንደማይፈቀድ፤ ከነዚህ ውስጥ አንዳቸውም አንዱን አሁን አንዱን ዘግይቶ መሰጣጠት እንደማይፈቀድና ከመቀባበል በፊት መለያየትም አለመፈቀዱን ነቢዩ የአላህ ሶዋትና ሰላም (ሶለሏሁ ዓለይሂ ሰለም) ማውሳታቸውን ዑመር ገለፁ።فوائد الحديث
እዚህ ሐዲሥ ውስጥ የተጠቀሱት የገንዘብ አይነቶች አምስት ናቸው: ወርቅ፣ ብር፣ ስንዴ፣ ገብስና ተምር ናቸው። ወርቅን በወርቅ እንደመገበያየት አይነቱ ግብይቱ ተመሳሳይ አይነቶችን በመለዋወጥ ከሆነ ግብይቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ ሁለት መስፈርቶች ሊሟሉ ይገባል: በውሉ ስፍራ ላይ መለዋወጥና ሚዛኑም መመሳሰል ይገባዋል። ይህ ካልሆነ ግን ግብይቱ የማበላለጥ አራጣ ይሆናል። በስንዴ ብር መለዋወጥን ይመስል ግብይቱ የሚካሄደው በተለያዩ የገንዘብ አይነቶች ከሆነ ግን ግብይቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ አንድ መስፈርት ነው ያለው: እርሱም በውሉ ስፍራ ዋጋውን መቀባበል ነው። ያለበለዚያ ግን የማዘግየት አራጣ ይሆናል።
የውሉ ስፍራ በማለት የተፈለገበት: ተቀምጠውም ሆነ፣ እየሄዱም ሆነ፣ እየጋለቡም ሆነ የመገበያያው ስፍራውን ነው። ከግብይይቱ ሲለያዩ በማለት የተፈለገው ደግሞ በተለምዶ ተገበያዮች በመካከላቸው ተለያዩ ተብሎ የሚታሰበው ሲከሰት ማለት ነው።
ሐዲሡ ውስጥ ያለው ክልከላ ለመገበያያ የተበጀውንም ይሁን ሌሎቹን የወርቅና የብር አይነቶችን ባጠቃላይ ያካትታል።
በዚህ ዘመን የምንጠቀመው መገበያያ ገንዘብም ምንዛሬም በወርቅና ብር ላይ ግዴታ የሆነው ነገር እርሱም ላይ ግዴታ ይሆናል። ማለትም አንድን ጥሬ ገንዘብ በሌላ ጥሬ ገንዘብ መመንዘር ከፈለግክ ሪያልን በዲርሃም መመንዘር ይመስል ሁለቱ ወገኖች በተስማማቸው መልኩ ማበላለጥ ይፈቀድላቸዋል። ነገር ግን ግብይቱ በተፈፀመበት ስፍራ (ወዲያውኑ) መለዋወጥ ግዴታ ነው። ያለበለዚያ ስምምነታቸውም ተቀባይነት አይኖረውም፤ ግብይታቸውም ክልክል የሆነው አራጣዊ ግብይት ይሆናል።
አራጣዊ ግብይት አይፈቀድም። ሁለቱ ወገኖች ቢስማሙ እንኳ ስምምነቱም ተቀባይነት የለውም። እስልምና ግለሰብም ይሁን ማህበረሰብ ሐቁን ችላ ቢልም እንኳ ሐቁን ይጠብቅለታልና።
የቻለ ሰው መጥፎን ነገር መከልከልና ማውገዝ እንዳለበት እንረዳለን።
ዑመር ቢን አልኸጧብ እንዳደረጉት መጥፎን በምናወግዝበት ወቅት ማስረጃን መጥቀስ እንደሚገባ እንረዳለን።
التصنيفات
አራጣ