إعدادات العرض
ሐጅና ዑምራን አከታትላችሁ አድርጉ። ወናፍ የብረትን፣ የወርቅንና የብርን ቆሻሻ እንደሚያስወግደው እነርሱም ድህነትንና ወንጀልን ያስወግዳሉ። ተቀባይነት ላለው ሐጅ ከጀነት በቀር…
ሐጅና ዑምራን አከታትላችሁ አድርጉ። ወናፍ የብረትን፣ የወርቅንና የብርን ቆሻሻ እንደሚያስወግደው እነርሱም ድህነትንና ወንጀልን ያስወግዳሉ። ተቀባይነት ላለው ሐጅ ከጀነት በቀር ሌላ ምንም ምንዳ የለውም።
ከዓብደላህ ቢን መስዑድ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "ሐጅና ዑምራን አከታትላችሁ አድርጉ። ወናፍ የብረትን፣ የወርቅንና የብርን ቆሻሻ እንደሚያስወግደው እነርሱም ድህነትንና ወንጀልን ያስወግዳሉ። ተቀባይነት ላለው ሐጅ ከጀነት በቀር ሌላ ምንም ምንዳ የለውም።"»
[ሶሒሕ ነው።]
الترجمة
العربية Tiếng Việt Bahasa Indonesia Nederlands Kiswahili অসমীয়া English ગુજરાતી සිංහල Magyar ქართული Hausa Română ไทย Português मराठी ភាសាខ្មែរ دری বাংলা Kurdîالشرح
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የሐጅና የዑምራን አምልኮ አቀራርቦ በመፈፀምና ከቻሉ ሳያቆራርጡ በመፈፀም ላይ አነሳሱ። ምክንያቱንም ሲገልፁ ብረትን በወናፍ እሳት መንፋት ብረቱ ላይ የተቀላቀለውን ባዕድ የማዕድን ቆሻሻ ለማስወገድ ምክንያት እንደሆነው ሁሉ እነርሱንም መፈፀም ድህነትንና ወንጀልን እንዲሁም ወንጀል በቀልብ ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖ ለማስወገድ ምክንያት መሆናቸውንም ገለፁ።فوائد الحديث
ሐጅና ዑምራን የማከታተል ትሩፋትና በርሱም ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
ሐጅና ዑምራን ማከታተል የሀብትና ወንጀልን የማስማር ሰበብ እንደሆነ እንረዳለን።
ሙባረክ ፉሪ እንዲህ ብለዋል: "(ድህነትን ያስወግዳሉ።) በማለት የተፈለገው በእጅ በሚገኝ ሀብት የሚወገደውን ውጫዊውን ድህነትም ሊሆን ይችላል። የቀልብ መብቃቃትን በማግኘት የሚወገደውን ውስጣዊ ድህነትም ሊሆን ይችላል።"
التصنيفات
የሐጅና ዑምራ ትሩፋት