إعدادات العرض
ሲበዛ ያሰከረ ነገር ትንሹ ክልክል ነው።
ሲበዛ ያሰከረ ነገር ትንሹ ክልክል ነው።
ከጃቢር ቢን ዐብደሏህ ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፡ «የአሏህ መልዕክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል፡ "ሲበዛ ያሰከረ ነገር ትንሹ ክልክል ነው።"
[ሐሰን ነው።] [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية Tiếng Việt Bahasa Indonesia Nederlands Kiswahili English অসমীয়া ગુજરાતી සිංහල Magyar ქართული Hausa Română ไทย Português తెలుగు मराठी ភាសាខ្មែរ دری বাংলা Kurdîالشرح
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አብዝቶ ሲወሰድ አይምሮን የሚያስወግድ ማንኛውም የሚጠጣ ወይም የሚበላ ነገር ሁሉ አይምሮን የሚያስወግድበትን ያህል መጠን የማይደርስ ትንሽ እንኳ መውሰድ ክልክል መሆኑን ገለፁ።فوائد الحديث
ሸሪዓ የሰዎችን አይምሮ እንደጠበቀ እንረዳለን።
ወደ ክልክል የሚያደርሱ መንገዶችን መዝጋት የሚለው መርህ በትክክል የሚተገበር መሆኑን እንረዳለን። ይህም ሁሉንም ወደዚህ ቆሻሻ ነገር የሚያደርሱን መንገዶች ሁሉ በመዝጋት ነው።
አስካሪን ነገር በጥቂቱ እንኳ መውሰድ ወደ ስካር መንገድ የሚያደርስ ስለሆነ መከልከሉን እንረዳለን።
በትንሹም ሆነ አብዝቶ ቢወሰድ የማያሰክር ነገር ክልክል አለመሆኑን እንረዳለን።
التصنيفات
የተከለከሉ መጠጦች