ሽርጡን ከቁርጭሚቶች ዝቅ ያደረገ እሳት ውስጥ ነው።

ሽርጡን ከቁርጭሚቶች ዝቅ ያደረገ እሳት ውስጥ ነው።

ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ሽርጡን ከቁርጭሚቶች ዝቅ ያደረገ እሳት ውስጥ ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ወንዶች ከወገባቸው በታች ያለ አካላቸውን የሚሸፍነውን ልብስ ወይም ሱሪያቸውን ወይም ከዛም ውጪ የሆነውን ልብስ ከቁርጭምጭሚታቸው በታች ዝቅ ከማድረግ አስጠነቀቋቸው። ሽርጡን ከቁርጭምጭሚቱ በታች ዝቅ ያደረገው ሰውዬም ለሰራው ስራ ቅጣት ይሆነው ዘንድ እግሩ እሳት ውስጥ ይሆናል።

فوائد الحديث

ወንዶች ልብስን ከቁርጭምጭሚት በታች ከማርዘም መከልከላቸውንና ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል እንደሆነም እንረዳለን።

ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ሽርጥን ማስረዘም ከሚለው ጥቅል ውስጥ በአስገዳጅ ምክንያት ያስረዘመ ተነጥሎ ይወጣል። ለምሳሌ ቁርጭምጭሚቱ ላይ ቁስል ወጥቶበት ዝንቦች የሚያውኩትና ከሽርጡ ውጪ ሌላ የሚሸፍንለት ልብስ (ፋሻ) ያላገኘ ሰውን ይመስል።"

ይህ ብይን ወንዶችን ብቻ የሚመለከት ነው። ምክንያቱም ሴቶች ልብሶቻቸውን ከቁርጭምጭሚታቸው በታች የክንድ ርዝመት ያህል እንዲለቁ ታዘዋልና።

التصنيفات

ልብስና ጌጥ