إعدادات العرض
አንድ ሰው ሌላን ሰው በአመፀኝነትም ሆነ በከሃዲነት አያነውረውም ባለቤቱ እንደዚያ ካልሆነ ወደርሱ ብትመለስ እንጂ።
አንድ ሰው ሌላን ሰው በአመፀኝነትም ሆነ በከሃዲነት አያነውረውም ባለቤቱ እንደዚያ ካልሆነ ወደርሱ ብትመለስ እንጂ።
ከአቡዘር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምተዋል: "አንድ ሰው ሌላን ሰው በአመፀኝነትም ሆነ በከሃዲነት አያነውረውም ባለቤቱ እንደዚያ ካልሆነ ወደርሱ ብትመለስ እንጂ።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Português සිංහල Nederlands Tiếng Việt অসমীয়া ગુજરાતી Kiswahili پښتو ไทย മലയാളംالشرح
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለሌላ ሰው "አንተ አመፀኛ" ወይም "አንተ ከሃዲ" ያለ ሰው ያ ሰው እንደተናገረው ካልሆነና ለተጠቀሰው ባህሪ የተገባ ካልሆነ ንግግሩ ወደራሱ የሚመለስ መሆኑን አስጠነቀቁ። እንደተናገረው ከሆነ ግን በተናገረው ንግግር እውነተኛ ስለሆነ አንድም ነገር ወደርሱ አይመለስበትም።فوائد الحديث
ያለ ሸሪዓዊ ተጨባጭ ማረጋገጫ ሰዎችን በክህደት ወይም በአመፀኝነት ማነወር ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
በሰዎች ላይ በሚሰጡ ፍርዶች ማረጋገጥ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
ኢብኑ ደቂቅ አልዒድ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ከሙስሊሞች መካከል አንድን ሰው እርሱ ከሃዲ ሳይሆን ከሃዲ ለሚል ሰው ትልቅ ዛቻ ነው። ይህም ትልቅ ጣጣ ነው።"
ኢብኑ ሐጀር አልዓስቀላኒይ እንዲህ ብለዋል: «ነገር ግን በዚህ ንግግሩ እውነቱን ከሆነ አመፀኛ ወይም ከሃዲ አይሆንም ሲባል "አንተ አመፀኛ" በሚለው ንግግሩ ምንም ወንጀለኛ ሊሆን አይችልም የሚለውን አያሲዝም። ይልቁንም ይህ ሁኔታ በዝርዝር መታየት ይገባዋል። "አንተ አመፀኛ" ሲለው የፈለገበት እርሱን መምከር ወይም የርሱን ሁኔታ ለሌሎች በመግለፅ ሌሎችን መምከር ከሆነ ይፈቀዳል። እርሱን ማነወር፣ ወንጀል መስራቱ እንዲታወቅ ለማድረግና ለመጉዳት ብቻ አስቦ ከሆነ ግን አይፈቀድም። ምክንያቱም እርሱ የታዘዘው እንዲሸሽግለት፣ በመልካም መልኩ እንዲያስተምረውና እንዲመክረው ነው። ይህንን በልስላሴ ማስተማር እስከቻለ ድረስ በሀይል መፈፀሙ አይፈቀድለትም። በሀይል መምከሩ አብዛኛው ሰው እልህ ውስጥ ገብቶ እንደሚያደርገው እንዲጠምና በዛ ወንጀል ላይ እንዲዘወትር ምክንያት ይሆናልና። በተለይ አዛዡ ከታዛዡ በደረጃ ዝቅ ያለ የሆነ ጊዜ ይህ ይከሰታል።»