إعدادات العرض
ረመዳን የገባ ጊዜ የጀነት በሮች ይከፈታሉ፤ የእሳት በሮችም ይዘጋሉ፤ ሰይጣኖችም ይጠፈነጋሉ።
ረመዳን የገባ ጊዜ የጀነት በሮች ይከፈታሉ፤ የእሳት በሮችም ይዘጋሉ፤ ሰይጣኖችም ይጠፈነጋሉ።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦ "ረመዳን የገባ ጊዜ የጀነት በሮች ይከፈታሉ፤ የእሳት በሮችም ይዘጋሉ፤ ሰይጣኖችም ይጠፈነጋሉ።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी සිංහල Hausa Kurdî Português Tiếng Việt অসমীয়া Nederlands Kiswahiliالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የረመዷን ወር የገባ ጊዜ ሶስት ነገሮች እንደሚከሰቱ ተናገሩ:- አንደኛ: የጀነት በሮች ይከፈታሉ። ከጀነት በሮችም አንድም በር አይዘጋም። ሁለተኛ: የእሳት በሮች ይዘጋሉ። አንድም የእሳት በር አይከፈትም። ሶስተኛ: ሰይጣኖችና አመፀኛ ጋኔኖች በሰንሰለት ይጠፈነጋሉ። ከረመዷን ውጪ ይደርሱበት ወደነበረው አይደርሱም። ይህ ሁሉ ለዚህ ወር ልቅና፣ ከሶላት፣ ከሶደቃ፣ ከዚክር፣ ቁርአን ከመቅራትና ከዛም ውጪ ያሉ አምልኮዎች በማብዛት ላይና ከወንጀሎችና ከሀጢአቶች በመራቅ ላይ ሰሪዎችን ለማነሳሳት ነው።فوائد الحديث
የረመዷን ወር ደረጃን እንረዳለን
ይህ የተከበረ ወር የአምልኮና የመልካም ተግባር ወቅት ከመሆኑ አኳያ ይህ ሐዲሥ ለጾመኞች ብስራት ነው።
ረመዷን ውስጥ ሸይጣኖች መጠፍነጋቸው የትኛውም ለአቅመ አዳም የደረሰ ሰው ወንጀል ለመስራት ምክንያት እንደሌለው ለመጠቆም ነው። "ሸይጣኖች ወደ አንተ እንዳይቀርቡ ስለተጠበቅክ አምልኮ ለመተውህና ወንጀልን ለመስራትህ እነርሱን ምክንያት እንዳታደርግ።" የተባለ ነው የሚመስለው።
ቁርጡቢይ እንዲህ ብለዋል: «"በረመዳን ውስጥ ብዙ ክፋትና ወንጀሎች ሲከሰት እንዴት እናያለን? ሸይጣኖች ቢታሰሩ ኖሮ ይህ አይከሰትም ነበር።" ቢባል። መልሱ: ክፋቶችና ወንጀሎች የሚያንሱት መስፈርቶቹን የጠበቀና ስነስርዓቱን ያሟላን ጾም ከጾሙ ሰዎች ላይ ነው። ወይም የሚታሰሩት በአንዳንድ ዘገባዎች ቀደም ተብሎ እንደተጠቀሰው ሁሉም ሳይሆኑ አመፀኛ የሆኑት የተወሰኑ ሸይጣኖች ብቻ ናቸው። ወይም በሐዲሡ የተፈለገው ክፋቶች እንደሚያንሱ መጥቀስ ነው። ይህም ደግሞ በገሃድ የሚታይ ነገር ነው። ከሌላ ጊዜ በተለየ ወንጀሎች በረመዷን መከሰታቸው እጅግ የመነመነ ነውና። በተጨማሪም ሁሉም ሸይጣኖች በመታሰራቸው ክፋትና ወንጀል አይከሰትም የሚለውን አያሲዝም። ወንጀል ለመስራት እንደ ቆሸሸች ነፍስ፣ መጥፎ ልምዶችና የሰው ሸይጣኖችን የመሰሉ ከጂን ሸይጣን ውጪ ያሉ ሌሎች ምክንያቶችም ስላሉ።
التصنيفات
የጾም ትሩፋት