إعدادات العرض
የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በሶስት ወቅቶች ላይ ከመስገድ ወይም ሟቾቻችንን ከመቅበር ይከለክሉን ነበር።
የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በሶስት ወቅቶች ላይ ከመስገድ ወይም ሟቾቻችንን ከመቅበር ይከለክሉን ነበር።
ከዑቅባህ ቢን ዓሚር አልጁሀኒይ ረዲየሏሁ ዐንሁ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ "የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በሶስት ወቅቶች ላይ ከመስገድ ወይም ሟቾቻችንን ከመቅበር ይከለክሉን ነበር። ፀሃይ በምትወጣ ጊዜ ከፍ እስክትል ድረስ፤ ፀሐይ እኩኩል (መሃል አናት ላይ) በምትሆን ወቅት የሚቆም ሰው (ያለ ምንም ጥላ) የሚቆም ከሆነበት ወቅት ፀሐይ ወደ መግቢያዋ እስክትዘነበል ድረስ፤ ፀሃይ ለመግባት በምትዘነበልበት (በምትቀርብበት) ወቅት እስክትገባ ድረስ ነው።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Português Tiếng Việt Kiswahili Nederlands অসমীয়া ગુજરાતી සිංහල Magyar ქართული Română ไทย తెలుగు मराठी ភាសាខ្មែរ دریالشرح
ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከቀኑ ክፍለ ጊዜ በሶስት ወቅቶች ላይ ሱና ሶላቶችን ከመስገድ ወይም ሟቾችን ከመቅበር ከለከሉ: የመጀመሪያው ወቅት: ፀሃይ በምትወጣ ጊዜ ነው። ይህም ገና መጀመሪያ ስትወጣ ነው። ክልከላውም የጦር ርዝመት ያህል ከፍ እስክትል ድረስ ነው። ቆይታውም እስከ ሩብ ሰአት አካባቢ ይገመታል። ሁለተኛው: ፀሐይ በሰማዩ መሃል ላይ በምትሆንበት ወቅት ነው። በዚህ ወቅትም በምስራቅም ሆነ በምዕራብ አቅጣጫ ጥላ አይኖራትም። ክልከላውም ከሰማዩ መሃል ወደ ምዕራብ ዘንበል እስክትል ድረስ ነው። በዚህም ጊዜ ጥላ ወደ ምስራቅ አቅጣጫ ዘንበል ማለት ይጀምራል። ይህም የዙህር ሶላት ወቅት የሚጀምርበት ወቅት ነው። ይህ የክልከላው ወቅትም አጭር ጊዜ ነው። አምስት ደቂቃ አካባቢ ይገመታል። ሶስተኛው: ፀሐይ ለመግባት በምትዘነበልበትና በምትጀምርበት ወቅት ነው። ክልከላውም እስክትገባ ድረስ ነው።فوائد الحديث
ይህ ሐዲሥም ይሁን ሌሎችም ሐዲሦች እንደሚጠቁሙት ሶላት ክልክል የሆነባቸው ወቅቶች: አንደኛ: ከፈጅር ሶላት በኋላ ፀሐይ እስክትወጣ ድረስ፤ ሁለተኛ: ፀሐይ በምትወጣ ወቅት በዓይናችን ግምት የጦር ያህል ከፍ እስክትል ድረስ ማለትም በግምት አስራ አምስት ደቂቃ አካባቢ፤ ሶስተኛ: ፀሐይ መሃል አናት ላይ በምትሆንበት ወቅት ማለትም የሆነ ሰው ሲቆም (በእግሩ ስር እንጂ) በምስራቁም በምዕራቡም በኩል የተዘረጋ ጥላ በማይኖርበት ወቅት ፀሐይ እስክትዘነበል ድረስ ነው። አንዳንዶችም አምስት ደቂቃ አካባቢ እንደሆነ ገምተዋል፤ አራተኛ: ከዐስር ሶላት በኋላ ፀሃይ እስክትገባ ድረስ፤ አምስተኛ: ፀሐይ ወደ ቢጫ ከተቀየረችበት ወቅት ጀምሮ እስክትገባ ድረስ ነው።
በነዚህ በተከለከሉ አምስት ወቅቶች መስገድ መከልከሉን እንረዳለን። ግዴታ ሶላቶችና ምክንያት ያላቸው ሱና ሶላቶች ግን እዚህ ክልከላ ውስጥ አይካተቱም።
ሐዲሡ ውስጥ የተጠቀሱት እነዚህ ሶስት ጠባብ ወቅቶች እስኪደርስ ድረስ ሆን ብሎ አዘግይቶ መቅበር መከልከሉን እንረዳለን። ከነዚህ ወቅቶች ውጪ ግን በማንኛውም የቀኑም ይሁን የምሽቱ ክፍለ ጊዜ ላይ መቅበር እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
በመሰረቱ አንድ ሙስሊም በአላህ ስለታዘዘ ብቻ መታዘዝ ስለከለከለውም ብቻ መታቀብ አለበት። የትእዛዙ ጥበቡ እንዲህ ነው የክልከላው ምክንያት እንዲህ ነው ተብሎ ጥበቡ ወይም ምክንያቱ አልተገለፀልኝም በሚል ተገዢ መሆኑን አያቆምም። ሁሌም ታዛዥ መሆን የሚገባው ቢሆንም በነዚህ ወቅቶች ላይ ከመስገድ የመከልከሉ ጥበብ በሌሎች ሐዲሦች ተጠቅሷል: የመጀመሪያው: ፀሐይ ወደ መግቢያዋ ከመዘንበሏ በፊት መሃል ላይ ስትሆን ጀሃነም እጅግ ከፍተኛ በሆነ መልኩ የምትቀጣጠልበት ወቅት ነው። ሁለተኛ: ፀሐይ በምትወጣ ወቅትና በምትገባ ወቅት ከመስገድ የመከልከሉ ጥበብ ደግሞ ከአጋርያን ጋር መመሳሰል ስለሆነ ነው። አጋርያን ፀሐይ በምትወጣና በምትገባ ወቅት ለርሷ ይሰግዳሉና። ሶስተኛ: ከፈጅር ሶላት በኋላ ፀሐይ እስክትወጣ ድረስና ከዐስር ሶላት በኋላ ፀሐይ እስክትገባ ድረስ ከመስገድ የመከልከሉ ጥበብ ደግሞ ከከሃዲያን ጋር የመመሳሰሉን ጉዳይ ለመቁረጥና እነርሱ ፀሃይ ስትወጣና ስትገባ ለፀሃይ በመስገድ የሚፈፅሙትን ማጋራት አንድ ሙስሊም ከነርሱ ጋር እንዳይመሳሰል ወደርሱ የሚያዳርሰውንም መንገድ ለመዝጋት ነው።
التصنيفات
ሶላት ክልክል የሆነበት ወቅቶች