إعدادات العرض
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጫማ ሲለብሱ፣ ሲያበጥሩ፣ ሲፅዳዱና በሁሉም ጉዳያቸው ቀኝን መጠቀም ይወዱ ነበር።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጫማ ሲለብሱ፣ ሲያበጥሩ፣ ሲፅዳዱና በሁሉም ጉዳያቸው ቀኝን መጠቀም ይወዱ ነበር።
ከአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች፦ «ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጫማ ሲለብሱ፣ ሲያበጥሩ፣ ሲፅዳዱና በሁሉም ጉዳያቸው ቀኝን መጠቀም ይወዱ ነበር።»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt සිංහල ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî മലയാളം Kiswahili অসমীয়া ગુજરાતી دری Nederlands नेपाली پښتو ไทย Svenska Oromoo Кыргызча Română తెలుగు Lietuvių Malagasy ಕನ್ನಡ Српскиالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለማክበር የተገቡ የሆኑ ጉዳያቸውን ሲፈፅሙ በቀኝ መጀመርን ይወዱና ያስበልጡ ነበር። ከነዚህ ጉዳዮችም መካከል: ጫማ ሲያደርጉ በቀኝ እግር ይጀምራሉ፤ የጭንቅላታቸውን ፀጉርና ፂማቸውን ሲያበጥሩ፣ ሲቀቡና ሲያስውቡ በቀኝ ይጀምሩ ነበር፣ እጃቸውና እግራቸውን ዉዱእ ሲያደርጉም ቀኛቸውን ከግራ ያስቀድሙ ነበር።فوائد الحديث
ኢማሙ ነወዊይ እንዲህ ብለዋል፦ ይህ በሸሪዓ ውስጥ ቀጣይነት ያለው መርህ ነው። እርሱም ልብስና ሱሪ መልበስ፣ ጫማ መልበስ፣ መስጂድ መግባት፣ ጥርስን መፋቅ፣ መኳል፣ ጥፍርን መቁረጥ፣ ቀድሞ ቀመስን ማሳጠር፣ ፀጉር ማበጠር፣ የብብት ፀጉርን መንጨት፣ ጭንቅላትን መላጨት፣ ከሶላት ማሰላመት፣ የንፅህና አካላትን መታጠብ፣ ከሽንት ቤት መውጣት፣ መብላት፣ መጠጣት፣ መጨባበጥ፣ ጥቁሩን ድንጋይ ሰላም ማለትና የመሳሰሉትን በዚሁ ደረጃ ላይ ያሉ ክብርና ልቅና ያለውን ነገር በቀኝ መጀመር ይወደዳል። በተቃራኒው የሆነ ነገር ደግሞ ሽንት ቤት መግባት፣ ከመስጂድ መውጣት፣ መናፈጥ፣ ኢስቲንጃእ፣ ልብስና ሱሪ ማውለቅ፣ ጫማ ማውለቅና የመሳሰሉትን በግራ መጀመር ይወደዳል። ይህ ሁሉም ቀኝ ክብርና ልቅና ስላላት ነው።
"ቀኝን መጠቀም ይወዱ ነበር።" የሚለው: ድርጊቶችን በቀኝ እጅ፣ በቀኝ እግር ፣ በቀኝ ጎን፣ መጀመርንና ነገሮችን በቀኝ መቀባበልን ያካትታል።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: «ከዉዱእ አካላት መካከል ቀኝን ማስቀደም የማይወደድበት አካላቶች አሉ። እነርሱም ሁለቱ ጆሮዎች፣ ሁለቱ መዳፎችና ጉንጮች ሲሆኑ እነዚህ ሁሉ እኩል ነው የሚፀዱት። ይህንን ማድረግ የማይችል አካሉ የተቆረጠና መሰል (አንድ ላይ ማድረግ የማይችል) አይነት ከሆነ ቀኝን ያስቀድማል።»