ሱብሓነላህ! ሙእሚን'ኮ ነጃሳ አይሆንም።" አሉት።

ሱብሓነላህ! ሙእሚን'ኮ ነጃሳ አይሆንም።" አሉት።

ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «ከመዲና መንገዶች በአንዱ መንገድ ላይ እርሱ ጀናባ ላይ ሆኖ ሳለ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሲያገኙት ከእይታቸው ተደብቆ በመሄድ ገላውን ታጠበ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ፈልገው አጡት። በሚመጣበት ወቅትም "አቡ ሁረይራ ሆይ! የት ነበርክ?" አሉት። እርሱም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔን ያገኙኝ ጀናባ ላይ ሆኜ ስለነበር ገላዬን ሳልታጠብ ከርሶ ጋር መቀማመጥን ጠላሁ።" አላቸው። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ሱብሓነላህ! ሙእሚን'ኮ ነጃሳ አይሆንም።" አሉት።»

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአንድ የመዲና መንገድ ላይ አቡ ሁረይራን - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - አገኙ። አቡ ሁረይራም ጀናባ (የዘር ፈሳሽ ወጥቶት ገላውና ያልታጠበ) ላይ ስለነበር ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከነበረው ክብርና ልቅና የተነሳ በዚህ ሁኔታ ላይ ሆኖ ከርሳቸው ጋር መቀማመጡንና ማውራቱን ጠላ። ተደብቆ በመሄድም ታጠበና ከዚያም ተመልሶ መጣና ተቀመጠ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) የት ሄዶ እንደነበር ጠየቁት። የነበረበትንም ሁኔታ ነገራቸው። እርሱ በጀናባ ምክንያት ተነጅሶ ስለነበር ከርሳቸው ጋር መቀማመጥ ጠልቶ መሆኑን ነገራቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመደነቅ እንዲህ አሉት: አማኝ ሰው በማንኛውም ሁኔታ ላይ ቢሆን በሕይወትም ሆነ ሞቶ ንፁህ ነው አይነጀስም።

فوائد الحديث

ጀናባ የሚከለክለው ከሶላት፣ ቁርአንን ከመንካት፣ መስጂድ ውስጥ ከመቀመጥ ነው። ከሙስሊሞች ጋር ከመቀማመጥና ከነርሱ ጋር ከመገናኘት ግን አይከለክልም። ሙስሊም በጀናባ ምክንያት ነጃሳ አይሆንም።

አማኝ የሆነ ሰው በህይወትም ሆነ ሞቶ ንፁህ ነው።

የክብር፣ የእውቀትና የመልካምነት ባለቤቶችን ማላቅና ባማረ ሁኔታ ላይ ሁነን ከነርሱ ጋር መቀማመጥ እንደሚገባ እንረዳለን።

ተከታይ የሆነ ሰው የሚከተለውን አካል አስፈቅዶ መሄዱ የተደነገገ እንደሆነ እንረዳለን። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) አቡ ሁረይራን (አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና) እርሳቸው ሳያውቁ በመሄዱ አውግዘውታል። ይህም አስፈቅዶ መሄድ ካማሩ ስነ-ስርዓቶች መካከል አንዱ ስለሆነ ነው።

በመደነቅ ወቅት ሱብሓነሏህ (ጥርት ለአላህ የተገባ ነው) ማለት እንደሚገባ እንረዳለን።

አንድ ሰው የሚያሳፍር የሆነን ነገር አስፈላጊ ሲሆን መናገሩ እንደሚፈቀድ እንረዳለን።

ከሃዲ ነጃስ ነው። ነገር ግን ነጃሳነቱ እምነተ ብልሹ ስለሆነ በመሆኑ ሕዋሳዊ (ውስጣዊ) ነው።

ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "በተጨማሪ ከዚህ ሐዲሥ ከምንወስዳቸው ቁምነገሮች መካከል: ከመልካም ስነስርዓት መካከል አንድ ዓሊም ተከታዩ ስህተት ላይ ወድቋል ብሎ የፈራውን ነገር ሲመለከት ጠይቆት ትክክሉን በመንገር ብይኑን ማብራራት እንዳለበት ነው። አላህ ነው አዋቂው።"

التصنيفات

ነጃሳን ማስወገድ, ትጥበት