إعدادات العرض
ጀናዛን ከመሸኘት ተከልክለናል። አፅንዖት ሰጥተው ግን አልከለከሉንም።
ጀናዛን ከመሸኘት ተከልክለናል። አፅንዖት ሰጥተው ግን አልከለከሉንም።
ከኡሙ ዐጢየህ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "ጀናዛን ከመሸኘት ተከልክለናል። አፅንዖት ሰጥተው ግን አልከለከሉንም።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî Tiếng Việt Magyar ქართული Kiswahili සිංහල Română অসমীয়া ไทย मराठी ភាសាខ្មែរ دریالشرح
ኡሙ ዐጢየህ አልአንሷሪየህ (አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና) ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሴቶች ጀናዛን ለመሸኘት አብረው ከመሄድ እንደተከለከሉ ተናገረች። ይህም ለነርሱም ይሁን በነርሱ ምክንያት ፈተና ይከሰታል ተብሎ ስለተፈራና ትእግስታቸው ያነሰ ስለሆነ ነው። ቀጥላም (አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና) ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሌሎች ክልከላዎች ላይ እንደሚያከብዱት ይህንን ግን ክብደት ሰጥተው አልከለከሉም አለች።فوائد الحديث
ሴቶች ጀናዛን ከመሸኘት መከልከላቸውን እንረዳለን። ይህም ጀናዛው ወደሚሰናዳበትም ወደሚሰገድብትም ይሁን ወደ መቃብር ስፍራ ሲሄድ ያለውን መከተል ሁሉ የሚያካትት ክልከላ ነው።
የክልከላው ምክንያትም ሴቶች እንደዚህ አይነት የሚያሳዝን ሁኔታዎችና ልብ የሚነካ አጋጣሚዎችን መቋቋም ስለማይችሉ በዚህም ሰበብ ምንአልባት ግዴታቸው የሆነውን ትእግስት የሚፃረር ማማረርና ትእግስት ማጣት ሊታይባቸው ስለሚችል ነው።
ክልከላ በመሰረቱ እርምነትን (ሐራምነትን) ነው የሚጠቁመው። ነገር ግን ኡሙ ዐጢየህ (አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና) በጊዜው ከነበረው የአነጋገር ሁኔታ ጀናዛን ከመሸኘት መከልከላቸው አፅንዖት የተሰጠው ቁርጥ ክልከላ እንዳልሆነ ተረዳች። ነገር ግን ጀናዛን የመሸኘት ክልከላው ጠንከር ያለ መሆኑን የሚጠቁሙ ይህ ሐዲሥ ከሚጠቁመው የበለጠ በርካታ ሐዲሦች መጥተዋል።