إعدادات العرض
በአማኞች ላይ ወይም በኡመቴ ላይ እንዳይከብዳቸው ብዬ ነው እንጂ በሁሉም ሶላቶች ወቅት መፋቂያ እንዲጠቀሙ አዛቸው ነበር።
በአማኞች ላይ ወይም በኡመቴ ላይ እንዳይከብዳቸው ብዬ ነው እንጂ በሁሉም ሶላቶች ወቅት መፋቂያ እንዲጠቀሙ አዛቸው ነበር።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "በአማኞች ላይ ወይም በኡመቴ ላይ እንዳይከብዳቸው ብዬ ነው እንጂ በሁሉም ሶላቶች ወቅት መፋቂያ እንዲጠቀሙ አዛቸው ነበር።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî Kiswahili සිංහල Nederlands Tiếng Việt ગુજરાતી অসমীয়া پښتو ไทย नेपाली മലയാളംالشرح
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከኡመታቸው መካከል አማኞች ለሆኑት እንዳይከብድባቸው ባይሰጉላቸው ኖሮ ከሁሉም ሶላቶች ጋር መፋቂያን መጠቀም ግዴታ ያደርጉት እንደነበር ተናገሩ።فوائد الحديث
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በኡመታቸው ላይ ያላቸው እዝነትና እንዳይከብድባቸውም የሚጠነቀቁላቸው መሆናቸውን እንረዳለን።
የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ትእዛዝ ሱና መሆኑን የሚጠቁም ማስረጃ እስካልመጣ ድረስ በመሰረቱ ግዴታ ነው።
ሁሉም ሶላት ዘንድ የመፋቅን ተወዳጅነትና ያለውን ትሩፋት እንረዳለን።
ኢብኑ ደቂቅ አልዒድ እንዲህ ብለዋል: «ወደ ሶላት በሚቆም ወቅት መፋቅ የተወደደበት ጥበብ ሶላት ወደ አላህ መቃረቢያ ወቅት ስለሆነ ነው። ይህ ደሞ አምልኮውን ማላቅህን ለማንፀባረቅ ሲባል የተሟላ ሁኔታንና ንፁህ መሆንን ይጠይቃል።»
የሐዲሡ ጥቅል ሀሳብ ፆመኛ እንኳን ቢሆን ፀሃይ ዘንበል ካለች በኋላም መፋቁ እንደሚወደድለት ያካትታል። (ፆመኛ ሁኖ) በዙህርና ዐስር ሶላት ወቅት መፋቅን ይመስል።
التصنيفات
የነቢዩ ሙሐመድ ስነ-ተፈጥሮ