إعدادات العرض
አላህ ዐዘ ወጀል በቀን ኃጢዓት የፈፀሙ እንዲፀፀቱ (ተውበት እንዲያደርጉ) በምሽት እጁን ይዘረጋል። በምሽት ኃጢዓት የፈፀሙ እንዲፀፀቱ (ተውበት እንዲያደርጉ) ደግሞ በቀን እጁን…
አላህ ዐዘ ወጀል በቀን ኃጢዓት የፈፀሙ እንዲፀፀቱ (ተውበት እንዲያደርጉ) በምሽት እጁን ይዘረጋል። በምሽት ኃጢዓት የፈፀሙ እንዲፀፀቱ (ተውበት እንዲያደርጉ) ደግሞ በቀን እጁን ይዘረጋል። ይህም ፀሀይ በመግቢያዋ በኩል እስክትወጣ ድረስ ቀጣይ ነው።
ከአቡ ሙሳ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "አላህ ዐዘ ወጀል በቀን ኃጢዓት የፈፀሙ እንዲፀፀቱ (ተውበት እንዲያደርጉ) በምሽት እጁን ይዘረጋል። በምሽት ኃጢዓት የፈፀሙ እንዲፀፀቱ (ተውበት እንዲያደርጉ) ደግሞ በቀን እጁን ይዘረጋል። ይህም ፀሀይ በመግቢያዋ በኩል እስክትወጣ ድረስ ቀጣይ ነው።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Português සිංහල دری অসমীয়া Tiếng Việt Svenska ไทย Yorùbá Кыргызча Kiswahili ગુજરાતી नेपाली Română മലയാളം Nederlands Oromoo తెలుగు پښتو Soomaali Kinyarwanda Malagasy ಕನ್ನಡ Српскиالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህ ከባሮቹ ንስሀቸውን እንደሚቀበል ተናገሩ። አንድ ባሪያ በቀን ወንጀል ሰርቶ በምሽት ንስሀ ከገባም አላህ ንስሀውን ይቀበለዋል። በምሽት ወንጀል ሰርቶ በቀን ንስሀ ከገባም አላህ ንስሀውን ይቀበለዋል። አሏህ ንስሀ ለሚገቡ ሰዎች እጁን የሚዘረጋውም በንስሀቸው ስለሚደሰትና ንስሀቸውንም ለመቀበል ነው። የዚህ አለም ፍፃሜን የምታሳውቀው የፀሀይ ከመግቢያዋ በኩል መውጣት እስኪከሰት ድረስም የንስሀ በር ክፍት ከመሆን አይወገድም። ፀሀይ በመግቢያዋ በኩል የወጣች ጊዜ ግን የንስሀ በር ይዘጋል።فوائد الحديث
የተውበት በር ክፍት እስከሆነ ድረስ ተቀባይነቷም ይቀጥላል። ፀሀይ ከመግቢያዋ በመውጣቷ ደግሞ በሩ ይዘጋል። ልክ እንደዚሁ ጣእረ ሞት - ማለትም ነፍስ ልትወጣ ጉሮሮ ጋር - ከመድረሱ በፊት ንስሀ መግባትም ይገባዋል።
በወንጀል ተስፋ መቁረጥ እንደማይገባ፤ የአላህ ይቅር ባይነትና እዝነት ሰፊ መሆኑን እንዲሁም የተውበት በርም ክፍት መሆኑን እንረዳለን።
የተውበት (ንስሀ) መስፈርቶች: የመጀመሪያው: ከወንጀሉ መውጣት ነው። ሁለተኛው: ወንጀሉን በመፈፀሙ መፀፀት ነው። ሶስተኛው: ወደ ወንጀሉ ዳግመኛ ላይመለስ መቁረጥ ነው። እነዚህ መስፈርቶች ግን የተጣሰው የአላህ መብቶች ብቻ ከሆነ ነው። ከፍጡራን ሐቆች ጋር የተያያዘ ወንጀል ከሆነ ግን ንስሀው ትክክለኛ እንዲሆን ይህን ሀቅ ወደ ባለቤቱ መመለስ ወይም ከባለቤቱ ይቅርታን ማግኘት ተጨማሪ መስፈርት ነው።
التصنيفات
ተውበት