إعدادات العرض
ጾመኛ መሆኑን ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ሰው ጾሙን ይሙላ። ያበላውና ያጠጣው አላህ ነውና።
ጾመኛ መሆኑን ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ሰው ጾሙን ይሙላ። ያበላውና ያጠጣው አላህ ነውና።
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ጾመኛ መሆኑን ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ሰው ጾሙን ይሙላ። ያበላውና ያጠጣው አላህ ነውና።"»
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî සිංහල Kiswahili Tiếng Việt অসমীয়া ગુજરાતી Nederlands മലയാളം ไทย Românăالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የግዴታ ጾም ወይም የሱና ጾም ፁሞ ጾመኛ መሆኑን ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ሰው ጾሙን ይሙላ እንዳያፈጥር ብለው ገለፁ። ምክንያቱም ማፍጠርን አስቦ ሳይሆን ይህ (በመርሳቱ ምክንያት) አላህ የሰጠው ያበላው ያጠጣው ሲሳይ ነውና።فوائد الحديث
ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ሰው ጾሙ ትክክለኛ መሆኑን እንረዳለን።
ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ሰው በምርጫው ስላልሆነ መብላቱ ጥፋተኛ አያደርገውም።
አላህ ለባሮቹ ያለውን እዝነትና ለነረሱ ማቅለሉን፣ ጭንቅና ችግርንም ከነርሱ ላይ ማንሳቱን ተረድተናል።
አንድ ጾመኛ ሶስት መስፈርቶች የተሟሉ ጊዜ ካልሆነ በቀር ጾሙን አይፈታም። አንደኛ: አውቆ መሆኑ ነው፤ የማያውቅ ከሆነ አይፈታም። ሁለተኛ: እያስታወሰ መሆን አለበት። ረስቶ ከሆነ የበላው ጾሙም ትክክለኛ ነው። (ሲያስታውስ እስከታቀበ ድረስ) በርሱም ላይ ምንም ቀዿእ አይኖርበትም። ሶስተኛ: ፈቅዶ መሆን አለበት። ተገዶ መሆን የለበትም። በምርጫው የሚያስፈታ ነገር መውሰድ አለበት።
التصنيفات
ጾምን የሚያበላሹ ነገሮች