ለይለቱል ቀድርን በረመዷን የመጨረሻ አስር ቀናቶች በጎደሎ ቁጥሮቹ ውስጥ ፈልጓት።

ለይለቱል ቀድርን በረመዷን የመጨረሻ አስር ቀናቶች በጎደሎ ቁጥሮቹ ውስጥ ፈልጓት።

ከዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ለይለቱል ቀድርን በረመዷን የመጨረሻ አስር ቀናቶች በጎደሎ ቁጥሮቹ ውስጥ ፈልጓት።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለይለቱል ቀድርን ለመፈለግ መልካም ስራዎችን በማብዛት መታገል እንደሚገባ አነሳሱ። ለይለቱል ቀድርም በሁሉም ዓመት ከረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት በጎዶሎው ምሽቶች መሆኗ ተስፋ ይደረጋል። እነርሱም: ሀያ አንደኛ፣ ሀያ ሶስተኛ፣ ሀያ አምስተኛ፣ ሀያ ሰባተኛና ሀያ ዘጠነኛ ሌሊቶች ናቸው።

فوائد الحديث

የለይለቱል ቀድርን ትሩፋትና እርሷን በመፈለግ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

ከአላህ ጥበብና እዝነት መካከል ሰዎች እርሷን ፍለጋ በአምልኮ ሲታገሉ ምንዳቸው እንዲጨምር ይህቺን ሌሊት መደበቁ ነው።

ለይለቱል ቀድር በረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ ነው። በጎዶሎዎቹ ቀናት መሆኑም ይበልጥ ተስፋ ይደረጋል።

ለይለቱል ቀድር ማለት ከረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ሌሊቶች መካከል አንዷ ናት። እርሷም አላህ ዐዘ ወጀል በነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ላይ ቁርአን ያወረደበት ሌሊት ናት። ይህችንም ሌሊት በበረከትና በደረጃዋ ታላቅነት ከአንድ ሺህ ወር የተሻለች አድርጓታል። ስለዚህም በዚህች ሌሊት መልካም ስራ መስራት ታላቅ ስፍራ ያለው ነው።

(ለይለቱል ቀድር) ተብላ የተጠራቸው ወይ ልቅና ከሚለው ቃል ተወስዶ ነው። (እከሌ ቀድሩ ታላቅ ነው።) ማለትም ልቅናው ከፍ ያለ ነው ማለት ነው። ልክ እንደዚሁ ቀድሯ ትልቅ የሆነችው ሌሊት ሲባል "ቀድር" የሚለው ቃል ሌሊት ለሚለው ቃል ገላጭ ይሆናል። ማለትም የላቀችዋ (የተከበረችዋ) ሌሊት ማለት ነው። ማለትም ደረጃዋ፣ ልቅናዋና ስፍራዋ የላቀ ማለት ነው። {እኛ (ቁርአንን) በተባረከው ምሽት አወረድነው።} [አድዱኻን:3] ወይም ደሞ (ተቅዲር) መወሰኛ ከሚለው ቃል ነው የተወሰደችው ቢባልም ያስኬዳል። ማለትም በዚህች ምሽት ውስጥ በአመት ውስጥ የሚከሰተው ነገር ይወሰናል። {በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል።} [አድዱኻን:4]

التصنيفات

የረመዿን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት