በመሃላው የሙስሊምን ሐቅ ያለአግባብ የወሰደ ሰው አላህ ለርሱ እሳትን ግድ አድርጎበታል፤ ጀነትንም በርሱ ላይ እርም አድርጓል።" አንድ ሰውዬም ለርሳቸው እንዲህ አለ፡ "የአላህ መልክተኛ…

በመሃላው የሙስሊምን ሐቅ ያለአግባብ የወሰደ ሰው አላህ ለርሱ እሳትን ግድ አድርጎበታል፤ ጀነትንም በርሱ ላይ እርም አድርጓል።" አንድ ሰውዬም ለርሳቸው እንዲህ አለ፡ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! (የማለበት ጉዳይ) ትንሽም እንኳ ብትሆን (ይቀጣልን)?" እርሳቸውም "የአራክ እንጨት ቢሆን እንኳ! (ይቀጣበታል።)

ከአቡ ኡማማህ ኢያስ ቢን ሠዕለበህ አልሓሪሢይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: «"በመሃላው የሙስሊምን ሐቅ ያለአግባብ የወሰደ ሰው አላህ ለርሱ እሳትን ግድ አድርጎበታል፤ ጀነትንም በርሱ ላይ እርም አድርጓል።" አንድ ሰውዬም ለርሳቸው እንዲህ አለ፡ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! (የማለበት ጉዳይ) ትንሽም እንኳ ብትሆን (ይቀጣልን)?" እርሳቸውም "የአራክ እንጨት ቢሆን እንኳ! (ይቀጣበታል።)"»

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የሙስሊምን ሐቅ እያወቀ ያለአግባብ ለመውሰድ ዋሽቶ በአላህ ከመማል አስጠነቀቁ። የዚህ ተግባር ቅጣቱም እሳት መግባትና ጀነት መነፈግ ነው። ይህም ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል አንዱ ነው። አንድ ሰውዬም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የተማለበት ነገር ትንሽ ብትሆን እንኳ?" አለ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "የወሰደው ለመፋቂያነት ከአራክ ዛፍ የሚወሰድ እንጨት እንኳ ብትሆን ይህን ቅጣት ይቀጣል።" አሉ።

فوائد الحديث

የሌሎችን ሐቅ መውሰድ መከልከሉን፤ ብታንስ እንኳ የሰዎችን ሐቅ ለባለቤቶቹ ለመስጠት መጣር እንደሚገባ፤ ዳኛ በስህተት የሚሰጠው ውሳኔ አንድ ሰው የራሱ ያልሆነን ሐቅ እንዲወስድ የተፈቀደ እንደማያደርግለት እንረዳለን።

ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "የሙስሊሞች ሐቅን ከባድነት እንረዳለን። እንዲሁም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "የአራክ እንጨት እንኳ ቢሆን!" ማለታቸው በትንሽና በትልቅ ሐቅ መካከልም (ከተጥያቂነት በኩል) ልዩነት እንደሌለው እንረዳለን።"

ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ቅጣት የሚመለከተው የሙስሊምን ሐቅ ያለአግባብ ወስዶ ከተውበት በፊት የሞተን ነው። ተውበት አድርጎ፣ በድርጊቱ ተፀፅቶ፣ ሐቁንም ወደ ባለቤቱ መልሶ ይቅርታውንም ጠይቆ፣ ወደመሰል ድርጊት ላይመለስም የቆረጠ ከሆነ ግን ወንጀለኝነቱ ከርሱ ላይ ተነስቶለታል።"

ቃዲ እንዲህ ብለዋል: "ሐዲሡ ውስጥ የሙስሊም ሐቅ በማለት ተለይቶ የተጠቀሰው ሐዲሡ የሚመለከታቸው እነርሱ ስለሆኑና በሸሪዓ የሚተዳደሩት እነርሱ ስለሆኑ ነው እንጂ ከሙስሊም ውጪ የሆኑ ሰዎችን ሐቅ መውሰድ ይቻላል ማለት አይደለም። ይልቁንም ብይኑ እንደሙስሊሙ ብይን ነው።"

ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ውሸት ማለት አውቆም ሆነ ረስቶ፣ ስላለፈ ጉዳይም ሆነ ስለወደፊት አንድን ነገር ካለበት እውነታ ተቃራኒውን ማውራት ነው።"

التصنيفات

መቀማት