ሙስሊም የሆነ ሰው የሚናዘዘው ነገር ኑሮት ኑዛዜው እርሱ ዘንድ የተፃፈች ካልሆነች በቀር ሶስት ቀናቶችን ማደር አይገባውም።

ሙስሊም የሆነ ሰው የሚናዘዘው ነገር ኑሮት ኑዛዜው እርሱ ዘንድ የተፃፈች ካልሆነች በቀር ሶስት ቀናቶችን ማደር አይገባውም።

ከኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ ነቢዩን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰማ: "ሙስሊም የሆነ ሰው የሚናዘዘው ነገር ኑሮት ኑዛዜው እርሱ ዘንድ የተፃፈች ካልሆነች በቀር ሶስት ቀናቶችን ማደር አይገባውም።" ዐብደላህ ቢን ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ይህንን ሲናገሩ ከሰማው ጀምሮ ኑዛዜዬ እኔ ዘንድ የተፃፈች ሆና እንጂ አንድም ምሽት አላደርኩም።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሙስሊም የሆነ ሰው ትንሽ ብትሆን እንኳ አንዳች የሚናዘዘው ሐቅ ወይም ገንዘብ ኖሮ ኑዛዜው እርሱ ዘንድ የተፃፈች ካልሆነች በቀር ሶስት ቀናትን ማደር እንደማይገባው ተናገሩ። ዐብደላህ ቢን ዑመርም ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ: " የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ይህንን ሲናገሩ ከሰማው ጀምሮ ኑዛዜዬ እኔ ዘንድ የተፃፈች ሆና እንጂ አንድም ምሽት አድሬ አላውቅም።"

فوائد الحديث

ኑዛዜ የተደነገገ መሆኑንና ኑዛዜውን ለማብራራት፣ የአላህን ትእዛዝ ለመተግበር፣ ለሞት ለመዘጋጀትና በሚያጠምደው ነገር ከመጠመዱ በፊት ኑዛዜውንና ኑዛዜው የሚውልበትን ቦታ እንዲያጤንበት መቻኮል እንደሚገባ እንረዳለን።

ኑዛዜ ማለት ትርጉሙ: ቃል ኪዳን ማለት ነው። ይኸውም ሰውዬው ከሞተ በኋላ ለአንድ ግለሰብ የተወሰነውን የገንዘቡን ክፍል እንዲያንቀሳቅስ ቃል መግባት ወይም ለአንድ ግለሰብ ትናንሽ ልጆቹን እንዲከታተል ቃል ማስገባት ወይም ይቆጣጠረው የነበረን ማንኛውም ስራ ቁጥጥሩን ለሆነ ግለሰብ ቃል መግባት ማለት ነው።

ኑዛዜ ሶስት ክፍሎች አሉት: 1- ተወዳጅ የሆነ ነው። እርሱም ከሞተ በኋላ ምንዳው እንዲደርሰው የተወሰነውን የገንዘቡን ክፍል በመልካምና በበጎ አድራጎት እንዲንቀሳቀስ መናዘዝ ነው። 2 - ግዴታ የሆነ ነው። እርሱም ያላወጣው ዘካ ወይም ከፋራና የመሳሰሉ በሸሪዓ መሰረት ግዴታ የሆኑበት የአላህም ሐቅ ሆነ ወይም እንደ እዳና አደራን መመለስ የመሰሉ የሰው ልጅም ሐቅ ቢሆን ያሉበትን ሐቆች መናዘዝ ነው። 3 - ክልክል የሆነ ነው። እርሱም ኑዛዜው ከገንዘቡ ከሲሶ ከፍ ካለ ወይም ለወራሽ የተናዘዘ ጊዜ ነው።

የኢብኑ ዑመርን ረዲየሏሁ ዐንሁ ደረጃና መልካም ስራን ለመተግባርና የጥበበኛውን ፈጣሪ ድንጋጌ ለመከተል የነበረውን ፍጥነት እንረዳለን።

ኢብኑ ደቂቅ አልዒድ እንዲህ ብለዋል: «ለሁለት ቀንና ሶስት ቀን ኑዛዜን ሳይፅፉ ማደር የተግራራው ችግርና ጭንቅን ለማስወገድ ሲባል ነው።»

አንገብጋቢ ጉዳዮች በመፃፍ ሊጠበቁ ይገባል። ምክንያቱም መፃፍ ሐቆችን መጠበቂያና ማረጋገጫ ነውና።

التصنيفات

ኑዛዜ