በዚህ መስጂዴ የሚሰገድ ሶላት ከርሱ ውጪ ከሚሰገዱ አንድ ሺህ ሶላቶች የተሻለ ነው። የተከበረው መስጊድ (መስጂደል ሐራም) ሲቀር።

በዚህ መስጂዴ የሚሰገድ ሶላት ከርሱ ውጪ ከሚሰገዱ አንድ ሺህ ሶላቶች የተሻለ ነው። የተከበረው መስጊድ (መስጂደል ሐራም) ሲቀር።

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በዚህ መስጂዴ የሚሰገድ ሶላት ከርሱ ውጪ ከሚሰገዱ አንድ ሺህ ሶላቶች የተሻለ ነው። የተከበረው መስጊድ (መስጂደል ሐራም) ሲቀር።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በርሳቸው መስጂድ የሚሰገድ ሶላትን ደረጃ ገለፁ። እርሱም መካ ውስጥ ከሚገኘው ከተከበረው መስጂድ ውጪ ምድር ላይ በሚገኙ መስጂዶች ከሚሰገድ ሶላት ሁሉ በአንድ ሺህ እጥፍ ይበልጣል። በተከበረው መስጂድ (መስጂደል ሐራም) የሚሰገድ ሶላት ግን በርሳቸው መስጂድ ከሚሰገድ ሶላትም ይበልጣል።

فوائد الحديث

በተከበረው መስጂድና በነቢዩ መስጂድ የሚሰገድ ሶላት ምንዳ እጥፍ ድርብ መሆኑን እንረዳለን።

በተከበረው መስጊድ የሚሰገድ ሶላት ከርሱ ውጪ በሚገኙ መስጂዶች ከሚሰገዱ ሶላቶች በመቶ ሺህ በላጭ ነው።

التصنيفات

Rulings of the Prophet's Mosque, የመስጊዶች ህግጋት