የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በፈጅር ሁለት ረከዓዎች ላይ {ቁል ያ አዩሃል ካፊሩን} እና {ቁል ሁወሏሁ አሐድ}ን አነበቡ።

የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በፈጅር ሁለት ረከዓዎች ላይ {ቁል ያ አዩሃል ካፊሩን} እና {ቁል ሁወሏሁ አሐድ}ን አነበቡ።

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው: "የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በፈጅር ሁለት ረከዓዎች ላይ {ቁል ያ አዩሃል ካፊሩን} እና {ቁል ሁወሏሁ አሐድ}ን አነበቡ።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በፈጅር ሱና ሶላት ላይ ከፋቲሓ ቀጥለው በመጀመሪያው ረከዓ {ቁል ያ አዩሃል ካፊሩን} የ(አልካፊሩን) ምእራፍን በሁለተኛው ረከዓ ደግሞ {ቁል ሁወሏሁ አሐድ} የ(አልኢኽላስ) ምእራፍን መቅራት ይወዱ ነበር።

فوائد الحديث

በፈጅር ሱና ከፋቲሓ በኋላ እነዚህን ሁለት ምእራፎች መቅራት እንደሚወደድ እንረዳለን።

እነዚህ ሁለት ምዕራፎች የኢኽላስ ምዕራፎች በመባልም ይጠራሉ። በአልካፊሩን ምዕራፍ ውስጥ አጋርያኖች ከአላህ ውጪ ከሚገዙት ባጠቃላይ መጥራት፤ በተጨማሪ እነርሱ የሚሰሩት ማጋራት ስራቸውን ስላበላሸባቸው የአላህ ባሪያዎች እንዳልሆኑ፤ አላህ ብቻ መመለክ እንደሚገባው ትገልጻለች። በአልኢኽላስ ምዕራፍ ውስጥም አላህን መነጠል፤ ስራን ለርሱ ማጥራትና የአላህን ባህሪ መግለፅ ይገኝበታል።

التصنيفات

የሶላት አሰጋገድ