إعدادات العرض
(አላህን በማመፁ ምክንያት) አላህ ያስቀመጠው የቅጣት ወሰን ካልሆነ በቀር (ስርአት ለማስያዝ) ተብሎ አንድም ሰው ከአስር አለንጋ በላይ እንዳይገረፍ።
(አላህን በማመፁ ምክንያት) አላህ ያስቀመጠው የቅጣት ወሰን ካልሆነ በቀር (ስርአት ለማስያዝ) ተብሎ አንድም ሰው ከአስር አለንጋ በላይ እንዳይገረፍ።
ከአቡ ቡርዳህ አልአንሷሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ሲሉ ሰማ፦ "(አላህን በማመፁ ምክንያት) አላህ ያስቀመጠው የቅጣት ወሰን ካልሆነ በቀር (ስርአት ለማስያዝ) ተብሎ አንድም ሰው ከአስር አለንጋ በላይ እንዳይገረፍ።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Português മലയാളം Kurdî Tiếng Việt অসমীয়া Kiswahili Nederlandsالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በወንጀል ላይ ካልሆነ በቀር አንድም ሰው ከአስር አለንጋ በላይ መገረፉን ከለከሉ። ሐዲሡ ውስጥ የተፈለገው በቁጥር ተገድበው ከአላህና ከመልክተኛው የመጡ ግርፋቶች ወይም ምቶች ወይም ልዩ ቅጣቶችን አይደለም። ይልቁንም በሐዲሡ የተፈለገው ስርአት ለማስያዝ ሲባል ሚስትንና ልጅን መግረፍ ቢያስፈልግ ከአስር አለንጋ አይጨምር ማለት ነው።فوائد الحديث
አላህ ያዘዘባቸው ወይም የከለከላቸው የአላህ ድንበሮች እነርሱን ከመተላለፍ የሚያስጠነቅቁ የሆኑ ቅጣቶች አሏቸው። እነዚህ ቅጣቶችም ወይ ከራሱ ከአላህ የተወሰኑ ናቸው ወይም ደግሞ ዳኛው የተሻለ ነው ብሎ እንደሚያየው ይወሰናል።
ስርአት ማስያዣ ቅጣቶች ለማስፈራሪያና ትክክለኛውን አቅጣጫ ለማሳየት ያህል ቀለል ያሉ መሆን አለባቸው። የግድ መምታት ካስፈለገም ከአስር አለንጋ መጨመር የለበትም። በላጩም ያለዱላ ትክክለኛውን በመጠቆም፣ በማስተማር፣ በመምራትና በማበረታታት ስርአት ማስያዝ ነው። ይህም ትምህርቱን እንዲቀበሉና መማማሩም የለሰለሰ እንዲሆን የተሻለው መንገድ ነው። በነዚህ ሁኔታዎች የምናደርጋቸው ነገሮች ብዙ ጊዜ ይለያያሉ። ነገር ግን የተሻለውን አይቶ ማድረግ ተገቢ ነው።
التصنيفات
የቅጣት ህግጋት