إعدادات العرض
ከአዳኝ ወይም ከከብት ጠባቂ ውሻ ውጪ የሆነ ውሻን ያሳደገ ሰው በየቀኑ ከስራው ሁለት ቂራጦች ይቀነሱበታል።
ከአዳኝ ወይም ከከብት ጠባቂ ውሻ ውጪ የሆነ ውሻን ያሳደገ ሰው በየቀኑ ከስራው ሁለት ቂራጦች ይቀነሱበታል።
ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ: «"ከአዳኝ ወይም ከከብት ጠባቂ ውሻ ውጪ የሆነ ውሻን ያሳደገ ሰው በየቀኑ ከስራው ሁለት ቂራጦች ይቀነሱበታል።" ሳሊም እንዲህ አለ: አቡ ሁረይራም የእርሻ ባለቤት ነበርና "ወይም የእርሻ ጠባቂ ውሻ ካልሆነ" ይል ነበር።»
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Français ئۇيغۇرچە Hausa Português മലയാളം Kurdî Русский Tiếng Việt অসমীয়া Kiswahili Nederlands ગુજરાતી සිංහල ไทยالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለአደን ወይም ለከብቶችና አዝርዕት ጥበቃ ፈልጎ ካልሆነ በቀር ውሻን ከማሳደግ ከለከሉ። ከነዚህ ውጪ ለሆነ አላማ ያሳደገ ሰውም በየቀኑ ከስራው ሁለት ቂራጥ ምንዳ ይቀነስበታል። ቂራጥ ሲባል የተፈለገው መጠንን የሚያውቀውም አላህ ብቻ ነው።فوائد الحديث
አንድ ሙስሊም ከተገደቡለት አላማዎች ውጪ ውሻን ማሳደግ አይፈቀድለትም።
ውሻ ብዙ ጉዳትና ብልሽት ስለሚያስከትል ማሳደጉ የተከለከለ ነው። ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንደተረጋገጠው መላእክቶች ውሻ ያለበት ቤት ውስጥ አይገቡም። በተጨማሪም ውሻ ውስጥ ደጋግሞ በውሃና አፈር በማጠብ ካልሆነ በቀር የማይወገድ ከባድ ነጃሳ አለ።
التصنيفات
አደን