ከየሁሉም ሶላት መጠናቀቂያ ላይ 'አልላሁመ አዒንኒ ዓላ ዚክሪከ፣ ወሹክሪከ፣ ወሑስኒ ዒባደቲክ' ማለትን እንዳትተው አደራ እልሃለሁ።" አሉኝ።» ትርጉሙም (አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት፣…

ከየሁሉም ሶላት መጠናቀቂያ ላይ 'አልላሁመ አዒንኒ ዓላ ዚክሪከ፣ ወሹክሪከ፣ ወሑስኒ ዒባደቲክ' ማለትን እንዳትተው አደራ እልሃለሁ።" አሉኝ።» ትርጉሙም (አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት፣ በማመስገንና አምልኮህን በማሳመር ላይ አግዘኝ።)

ከሙዓዝ ቢን ጀበል (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ : «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጄን ያዙኝና እንዲህ አሉኝ: "ሙዓዝ ሆይ! ወላሂ እኔ እወድሃለሁ።" እንዲህም አሉ "ሙዓዝ ሆይ! ከየሁሉም ሶላት መጠናቀቂያ ላይ 'አልላሁመ አዒንኒ ዓላ ዚክሪከ፣ ወሹክሪከ፣ ወሑስኒ ዒባደቲክ' ማለትን እንዳትተው አደራ እልሃለሁ።" አሉኝ።» ትርጉሙም (አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት፣ በማመስገንና አምልኮህን በማሳመር ላይ አግዘኝ።)

[ሶሒሕ ነው።] [An-Nasaa’i - አቡዳውድ ዘግበውታል። - አሕመድ ዘግበውታል። - Maalik]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሙዓዝን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እጅ ያዙና ለርሱ እንዲህ አሉት: በአላህ እምልልሃለሁ እኔ እወድሃለሁ። ሙዓዝ ሆይ! በየሁሉም ሶላት መጨረሻ ላይ ይህን ማለት እንዳትተው አደራ እልሃለሁ። "አሏሁመ አዒኒ ዐላ ዚክሪከ" (አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት አግዘኝ) ወደ አምልኮ የሚያቃርበኝ በሆነ ንግግርና ተግባር ሁሉ አግዘኝ። "ወሹክሪከ" ፀጋን በማግኘትና መከራን በማስወገድም (አንተን ለማመስገን) አግዘኝ። ለአላህ ስራን በማጥራትና ነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመከተል (አምልኮህን በማሳመርም) አግዘኝ።

فوائد الحديث

ሰውን ለአላህ ብለን እንደምንወደው መንገር የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን።

በየሁሉም ግዴታና ሱንና ሶላቶች መጨረሻ ላይ ይህን ዱዓ ማድረግ መወደዱን እንረዳለን።

በነዚህ ጥቂት የዱዓ ቃላት ውስጥ ዱንያዊም አኺራዊም ፍላጎቶች አሉ።

ለአላህ ብሎ ከመውደድ ጥቅሞች መካከል በእውነት ላይ አደራ መባባል፣ መመካከር፣ በበጎና አላህን በመፍራት ላይ መተጋገዝ ይገኛሉ።

ጢቢይ እንዲህ ብለዋል: "አላህን ማውሳት የልብ መስፋት መግቢያ ነው። አላህን ማመስገን ደግሞ ተቀባይነት ላለው ፀጋ የሚያዳርስ ነው። አምልኮን ከማሳመር ተፈላጊው ጉዳይ ከአላህ ከሚያዘናጉ ነገሮች መለያየቱ ነው።"

التصنيفات

የሶላት አዝካሮች