ሰሑር ተመገቡ! በሰሑር ውስጥ በረከት አለ።

ሰሑር ተመገቡ! በሰሑር ውስጥ በረከት አለ።

ከአነስ ቢን ማሊክ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ሰሑር ተመገቡ! በሰሑር ውስጥ በረከት አለ።"»

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በሰሑር ጉዳይ አነሳሱ። እርሱም ለጾም ዝግጅት ሌሊቱ መጨረሻ ላይ መመገብ ነው። በሌሊቱ መጨረሻ ወቅት ለሰሑርና ለዱዓእ መቆም (በረከት) - ማለትም ብዙ ምንዳና አጅር - ያስገኛል። ለጾም ያነቃቃል፤ ክብደቱንም ያቀላል።

فوائد الحديث

ሰሑር መብላትና ሸሪዓዊ ትእዛዝን ተግባራዊ ማድረግ ይወደዳል።

ኢብኑ ሐጀር በፈትሑል ባሪይ ውስጥ እንዲህ ብለዋል: "በሰሑር የሚገኘው በረከት በበርካታ መንገዶች ይገኛል። ሰሑር መብላት ሱናን መከተል ነው፤ የመጽሐፉ ሰዎችን መቃረን ነው፤ ለአምልኮ ማጠናከሪያ ነው፤ ንቃትን የሚጨምር ነው፤ ረሃብ የሚያስከትለውን መነጫነጭ መከላከያ ነው፤ በዛን ወቅት ምፅዋት ለሚጠይቅ ሰው ወይም አብሮት ለሚበላ ሰው ለመመፅወት ምክንያት ነው፤ ዱዓ ተቀባይነት ያገኛል ተብሎ በሚታሰብበት በዚህ ወቅት ዱዓና ዚክር እንድናደርግ ምክንያት ነው፤ ከመተኛቱ በፊት ከመነየት ለተዘናጋ ሰው የጾሙን ኒያ እንዲነይት ምክንያት ነው።"

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ልብ ተደስቶ እንዲሰራውና የሸሪዓ ውበትን ለማሳወቅ ብያኔን ከጥበብ ጋር ማቆራኘታቸው የማስተማር ጥበባቸውን ያሳየናል።

ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: «ሰሑር ሰውዬው በሚበላው ወይም በሚጠጣው ትንሽ ነገርም ይገኛል።»

التصنيفات

የፆም ሱናዎች