إعدادات العرض
በኑ ኢስራኢሎችን ነቢያቶች ነበሩ ጉዳያቸውን የሚመሩት። አንድ ነቢይ በሞተ ቁጥር ሌላ ነቢይ ይተካ ነበር። ከኔ በኋላም ነቢይ የለም። ምትኮች (ኸሊፋዎች) ይኖራሉም ይበዛሉም።
በኑ ኢስራኢሎችን ነቢያቶች ነበሩ ጉዳያቸውን የሚመሩት። አንድ ነቢይ በሞተ ቁጥር ሌላ ነቢይ ይተካ ነበር። ከኔ በኋላም ነቢይ የለም። ምትኮች (ኸሊፋዎች) ይኖራሉም ይበዛሉም።
ከአቡ ሓዚም እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «አቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ዘንድ አምስት ዓመት ተቀምጫለሁ። ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብሎ ሲያወራም ሰምቸዋለሁ: "በኑ ኢስራኢሎችን ነቢያቶች ነበሩ ጉዳያቸውን የሚመሩት። አንድ ነቢይ በሞተ ቁጥር ሌላ ነቢይ ይተካ ነበር። ከኔ በኋላም ነቢይ የለም። ምትኮች (ኸሊፋዎች) ይኖራሉም ይበዛሉም።" ሶሐቦችም "ምን ያዙናል?" አሉ። እርሳቸውም "የመጀመሪያውን ቃል ኪዳን ሙሉ፤ ሐቃቸውንም ተወጡ። አላህም ለሰጣቸው ሀላፊነት ይጠይቃቸዋል።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt සිංහල ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Português தமிழ் Kiswahili অসমীয়া ગુજરાતી Nederlands മലയാളം ไทย Românăالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዛሬ ላይ ህዝቦችን የሚመሩት መሪዎችና ሹማምንት እንደሆኑት ያኔ በኒ ኢስራኢሎችን የሚመሯቸውና ጉዳያቸውንም በሀላፊነት የሚያዙት ነቢያቶች እንደነበሩ ተናገሩ። ብክለት በመካከላቸው በተንሰራፋ ቁጥርም ጉዳዩን የሚያስተካክልና የለወጡትን ህግ የሚያስወግድ ሌላን ነቢይ አላህ ይልክ ነበር። በነርሱ ላይ ያደርግ እንደነበረው የሚያደርግ ከኔ በኋላ የሚመጣ ነቢይ የለም። ከኔ በኋላ ምትኮች (ኸሊፋዎች) ነው የሚኖሩት እነርሱም በርካታ ይሆናሉ። በመካከላቸውም ልዩነትና ተቃርኖ ይከሰታል። ሶሐቦችም - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "ምን ያዙናል?" በማለት ጠየቁ። እርሳቸውም "ከአንዱ መሪ በኋላ ለሌላ መሪ ቃል ኪዳን ቢገባለት። የመጀመሪያው መሪ ቃልኪዳን ትክክለኛ ስለሆነ ታማኝ መሆን ያለባችሁ ለመጀመሪያው ነው። አንድ መሪ እያለ ለሁለተኛ መሪነት ቃል የተገባለት ግን ቃልኪዳኑ ተቀባይነት የሌለው ከንቱ ነው። እርሱም መሪነትን መፈለጉ ክልክል ነው። ለመሪዎች ሐቃቸውን ስጧቸው፣ ታዘዟቸው፤ ከወንጀል ውጪ በመታዘዝና በመስማትም ተኗኗሯቸው። በናንተ ላይ ለሚሰሩት ነገር አላህ ይጠይቃቸዋልም ይታሳሰባቸዋልም።"فوائد الحديث
ህዝቦች እንዲስተካከሉና ቀጥተኛውን መንገድ እንዲመሩ ጉዳያቸውን የሚያስኬድ ነቢይ ወይም ተተኪ መሪዎች ሊኖሩ የግድ ነው።
ከነቢያችን ሙሐመድ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በኋላ ሌላ ነቢይ የለም።
በሸሪዓዊ መንገድ መሪነቱ የተረጋገጠለትን ሰው አምፆ መውጣት መከልከሉን እንረዳለን።
በተመሳሳይ ወቅት ለሁለት ኸሊፋዎች (መሪዎች) የመሪነት ቃልኪዳን መግባት አይፈቀድም።
የመሪ ተጠያቂነት ትልቅ መሆኑን እንረዳለን። ምክንያቱም ስለሚመራቸው ህዝቦች አላህ ይጠይቀዋልና።
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "የዲን ጉዳይን ከዱንያ ጉዳይ ማስቀደም እንደሚገባ እንረዳለን። ይህም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የመሪን ሐቅ በመወጣት ያዘዙት እርሱን መታዘዝ ዲኑን የበላይ ስለሚያደርግና ፈተናና ሸርን ስለሚከላከል ነው። የራስን ሐቅ ከመፈለግ እንዲያዘገይ መታዘዙ ሐቁ ውድቅ ሆኗል የሚልን አያሲዝም። አላህ በመጪው አለም እንኳ ቢሆን ሐቁን እንደሚሞላለት ቃል ገብቷልና።"
የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ነቢይነት አንዱ ምልክት እንዳሉትም ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በኋላ መሪዎች መብዛታቸውና በኡመቱ ላይ አበጂዎችም መጥፎዎችም መሾማቸው ነው።
التصنيفات
ያለፉት ህዝቦች ሁኔታና ታሪክ