إعدادات العرض
የጁመዓ ቀን ልክ እንደ ጀናባ ትጥበት ከታጠበ በኃላ ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የግመል ቁርባን እንዳቀረበ ነው።
የጁመዓ ቀን ልክ እንደ ጀናባ ትጥበት ከታጠበ በኃላ ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የግመል ቁርባን እንዳቀረበ ነው።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ «የጁመዓ ቀን ልክ እንደ ጀናባ ትጥበት ከታጠበ በኃላ ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የግመል ቁርባን እንዳቀረበ ነው። በሁለተኛው ወቅት ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የከብት ቁርባን እንዳቀረበ ነው። በሶስተኛው ወቅት ማልዶ የሄደ ሰው ልክ ቀንዳም ሙክት ቁርባን እንዳቀረበ ነው። በአራተኛው ወቅት ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የዶሮ ቁርባን እንዳቀረበ ነው። በአምስተኛው ወቅት ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የእንቁላል ቁርባን እንዳቀረበ ነው። ኢማሙ ለኹጥባ የወጣ ጊዜ መላእክቶቹም ተግሳፁን ለመስማት ይገኛሉ።»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî සිංහල অসমীয়া Kiswahili Tiếng Việt ગુજરાતી Nederlands پښتو नेपाली മലയാളം Svenska ไทย Кыргызча Română Malagasy ಕನ್ನಡ Српски తెలుగుالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወደ ጁመዓ ሶላት ማልዶ የመሄድን ትሩፋት ተናገሩ። መማለዱም ፀሐይ ከወጣችበት ወቅት ጀምሮ ኢማሙ ለኹጥባ እስከሚመጣበት ወቅት ይቆያል። ይህም አምስት ወቅቶች ይኖሩታል። አከፋፈሉም ፀሐይ ከወጣችበት ወቅት ኢማሙ መስጂድ ገብቶ ለኹጥባ ሚንበር ላይ እስኪወጣ ያሉትን ወቅቶች ለአምስት በመክፈል ይገኛል። የመጀመሪያው: እንደ ጀናባ ትጥበት የተሟላ ትጥበትን ከታጠበ በኃላ በመጀመሪያው ወቅት ጁሙዓ ወደሚሰግድበት መስጂድ የሄደ ሰው ሲሆን ይህም ግመል ሶደቃ እንደሰጠ ሰው ነው። ሁለተኛው: በሁለተኛው ሰዓት የሄደ ሲሆን ይህም ከብት እንደመፀወተ ሰው ነው። ሶስተኛ: በሶስተኛው ሰዓት የሄደ ሰው ሲሆን ይህም ቀንዳም ሙክት እንደመፀወተ ሰው ነው። አራተኛ: በአራተኛው ሰዓት የሄደ ሰው ሲሆን ይህም ዶሮ እንደመፀወተ ሰው ነው። አምስተኛ: በአምስተኛው ሰዓት የሄደ ሰው ሲሆን ይህም እንቁላል እንደመፀወተ ሰው ነው። ኢማሙ ለኹጥባ የወጣ ጊዜም መስጂድ በር ላይ ተቀምጠው መስጂድ ለሚገቡ ሰዎች አንድ በአንድ የሚጽፉ መላዕክቶች መመዝገባቸውን ትተው ዚክርና ኹጥባ ለማዳመጥም ይመጣሉ።فوائد الحديث
የጁመዓ ቀን በመታጠብ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። ይህም ወደ ሶላት ከመሄድ በፊት ነው የሚፈፀመው።
ወደ ጁመዓ ሶላት በቀኑ የመጀመሪያ ሰአት ማልዶ የመሄድን ትሩፋት እንረዳለን።
ወደ መልካም ስራዎች በመቻኮል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
መላዕክቶች የጁመዓ ሶላትንና ኹጥባን ለማዳመጥ እንደሚገኙ እንረዳለን።
መላዕክቶች በመስጂድ በሮች ላይ ሆነው ወደ ጁመዓ ሶላት የሚመጡ ሰዎችን አንድ በአንድ ይፅፋሉ።
ኢብኑ ረጀብ እንዲህ ብለዋል: "የጁመዓ ቀን የታጠበና ቀጥሎ ማልዶ የሄደ ሰው" የሚለው አነጋገር ለጁመዓ ተብሎ መታጠብ የሚወደደው መጀመሪያው ጎህ ሲወጣ ሲሆን የመጨረሻው ደግሞ ወደ ጁመዓ ሲሄድ መሆኑን ይጠቁማል።