አላህ ወንድን ልጅ ወይም ሴትን ልጅ በመቀመጫ የተገናኘን ሰው (በእዝነት) አይመለከተውም።

አላህ ወንድን ልጅ ወይም ሴትን ልጅ በመቀመጫ የተገናኘን ሰው (በእዝነት) አይመለከተውም።

ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "አላህ ወንድን ልጅ ወይም ሴትን ልጅ በመቀመጫ የተገናኘን ሰው (በእዝነት) አይመለከተውም።"

[ሶሒሕ ነው።]

الشرح

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ወንድ ልጅን ወይም ሴት ልጅን በመቀመጫቸው የተገናኘን ሰው አላህ በእዝነት እይታ እንደማያየው ከባድ ዛቻን ገለፁ። ይህ ተግባርም ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል አንዱ ነው።

فوائد الحديث

ወንድ ልጅ ከወንድ ጋር መገናኘቱ (ግብረሰዶማዊነት) መፈፀሙ ከትላልቅ ወንጀሎች አንዱ ነው።

ሴትንም በመቀመጫዋ መገናኘት ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል አንዱ ነው።

(አላህ አይመለከተውም) ማለት የእዝነትና የርህራሄ እይታ አያየውም ማለት ነው እንጂ አጠቃላይ የሆነ እይታ ማለት አይደለም። አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ በርሱ ላይ አንዳችም ነገር አይሰወርም። አንድም ነገር ከርሱ እይታ አይርቅም።

ይህ ተግባር የሰውን ንፁህ ተፈጥሮ ስለሚፃረር፣ ዘርን ስለሚያሳንስ፣ የትዳርን ህይወት ስለሚያበላሽ፣ ጥላቻና ጠላትነትን ስለሚተክል፣ በቆሻሻ መንገድ ስለሚፈፀም በሰው ልጅ ከሚሰሩ ከትላልቅ ፀያፍና አደገኛ ተግባራት መካከል የሚመደብ ነው።

التصنيفات

የቅጣት ህግጋት