ከጠየቃችሁት የተሻለን ነገር አልጠቁማችሁምን? መኝታ ስፍራችሁን የያዛችሁ ጊዜ ወይም ወደ መኝታችሁ ስፍራ የተጠጋችሁ ጊዜ ሰላሳ ሶስት ጊዜ 'ሱብሓነላህ' ሰላሳ ሶስት ጊዜ 'አልሐምዱሊላህ'…

ከጠየቃችሁት የተሻለን ነገር አልጠቁማችሁምን? መኝታ ስፍራችሁን የያዛችሁ ጊዜ ወይም ወደ መኝታችሁ ስፍራ የተጠጋችሁ ጊዜ ሰላሳ ሶስት ጊዜ 'ሱብሓነላህ' ሰላሳ ሶስት ጊዜ 'አልሐምዱሊላህ' ሰላሳ አራት ጊዜ ደግሞ 'አላሁ አክበር' በሉ። ይህም ለናንተ ከአገልጋይ የተሻለ ነው።

ከዓሊ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ፋጢማ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ በወፍጮ ምክንያት እጇ ላይ ስለሚያጋጥማት ጉዳይ ለማማከር መጣች። እርሳቸው ዘንድ ባሪያ እንደመጣም ወሬ ደረሳት። ቤት ስትሄድም አላገኘቻቸውምና ይህንን ለዓኢሻ አወሳችላት። እርሳቸው ሲመጡም ዓኢሻ ለርሳቸው ነገረቻቸው። ዓሊይ እንዲህ አለ: «መኝታችን ላይ ሆነን ሳለ መጡ። ለመነሳት ስንዘጋጅም "ባላችሁበት ሁኑ" አሉንና መጥተው የእግራቸው ቅዝቃዜን ሆዴ እስኪሰማው ድረስ በኔና በርሷ መካከል መጥተው ተቀመጡና እንዲህ አሉ: "ከጠየቃችሁት የተሻለን ነገር አልጠቁማችሁምን? መኝታ ስፍራችሁን የያዛችሁ ጊዜ ወይም ወደ መኝታችሁ ስፍራ የተጠጋችሁ ጊዜ ሰላሳ ሶስት ጊዜ 'ሱብሓነላህ' ሰላሳ ሶስት ጊዜ 'አልሐምዱሊላህ' ሰላሳ አራት ጊዜ ደግሞ 'አላሁ አክበር' በሉ። ይህም ለናንተ ከአገልጋይ የተሻለ ነው።"»

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሴት ልጅ የሆነችው ፋጢማ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና በወፍጮ ስትፈጭ እጇ ላይ ስለሚደርስባት ምልክት ለነቢዩ ስሞታ አቀረበች። ወደ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ምርኮኛ የመጣ ጊዜ የቤት ስራን የሚተካላት ከነዚህ ምርኮኞች መካከል አንድ ሰራተኛ እንዲሰጧት ለመጠየቅም ወደርሳቸው ሄደች። ነገር ግን ቤት ውስጥ አላገኘቻቸውም። ዓኢሻን (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና ስለነበር ያገኘችው ለርሷ ነገረቻት። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቤታቸው ሲመጡም ፋጢማ ወደርሳቸው ሰራተኛን ልትጠይቃቸው መጥታ እንደነበር ነገረቻቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ፋጢማና ዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ዘንድ ፍራሻቸው ላይ ለእንቅልፍ እየተዘጋጁ ሳለ ቤታቸው መጡ። ዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ሆዱ ላይ የነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የእግር ቅዝቃዜ እስኪሰማው ድረስ በመካከላቸው ተቀመጡ። እንዲህም አሏቸው: ሰራተኛን እንድሰጣችሁ ከጠየቃችሁኝ ይልቅ የተሻለውን ነገር አላስተምራችሁምን? እነርሱም: እንዴታ አሏቸው። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: ምሽት ላይ የእንቅልፋችሁን ስፍራ የያዛችሁ ጊዜ ሰላሳ አራት ጊዜ 'አላሁ አክበር' በሉ። ሰላሳ ሶስት ጊዜ 'ሱብሓነላህ' በሉ። ሰላሳ ሶስት ጊዜም 'አልሐምዱሊላህ' በሉ። እነዚህ ዚክሮች ለናንተ ከሰራተኛም የተሻሉ ናቸው።

فوائد الحديث

በነዚህ የተባረኩ ዚክሮች ላይ መዘውተር እንደሚወደድ እንረዳለን። በሌላ ቦታ እንደተላለፈው ዓሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ይህን ነቢያዊ ምክር የ"ሲፊን ምሽት" እለት እንኳ አልተዋትም።

ይህ ዚክር በምሽት እንቅልፍ ላይ ካልሆነ በቀር አይባልም። ሙስሊም ላይ በሙዓዝ ቢን ሹዕባ የተዘገበው ቃል "ምሽት ላይ መኝታ ስፍራችሁን የያዛችሁ ጊዜ" በሚል ቃል ነው የተዘገበው።

አንድ ሙስሊም በመጀመሪያው የምሽት ክፍል እነዚህን ዚክሮች የረሳ ጊዜ ከዚያም በመጨረሻው የምሽት ወቅት አስታውሶ ቢላቸው ችግር የለውም። ይህን ሐዲሥ ያወራው ዓሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና የ "ሲፊን ምሽት" ላይ በመጀመሪያው ምሽት ይህን ዚክር ማለት እንደረሳና ከዚያም ከሱብሒ በፊት አስታውሶ እንዳለው ተናግሯል።

ሙሀለብ እንዲህ ብለዋል: «እዚህ ሐዲሥ ውስጥ አንድ ሰው ለራሱ ከዱንያ ይልቅ መጪውን አለም ማስቀደም ላይ ነፍሱን እንደሚገፋፋው ሁሉ ቤተሰቡንም የሚችሉት በሆነ ነገር ላይ መገፋፋት እንደሚገባው እንማርበታለን።»

ኢብኑ ሐጀር አልዐስቀላኒ እንዲህ ብለዋል: «በነዚህ ዚክሮች ላይ የዘወተረ ሰው ስራ ቢበዛበትም አይጎዳም። ድካም እንኳን ቢሰማው ውጥረት አይሆንበትም።»

ዐይኒ እንዲህ ብለዋል: «የተሻለ ነው የተባለው: ወይ ዚክሮቹ ተያያዥነታቸው አኺራዊ ሲሆን ሰራተኛ ግን ተያያዥነቱ ዱንያዊ ስለሆነ ሊሆን ይችላል። አኺራዊ የሆነ ደሞ የተሻለና ቀሪ ነውና። ወይም ደግሞ ከፍላጎቷ ጋር የተያያዘም ሊሆንም ይችላል። ይህም በነዚህ ዚክሮች አማካይነት ሰራተኛ ሊሰራላት ከሚችለው የበለጠ መስራት የምትችልበትን ሀይል ታገኛለች ማለት ነው።»

التصنيفات

ድንገተኛ የሆኑ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ የሚባሉ ዚክሮች