إعدادات العرض
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በሁለት ነገሮች መካከል ምርጫ ሲሰጣቸው ወንጀል እስካልሆነ ድረስ የሚመርጡት ገሩን ነው። ወንጀል ከሆነ ግን ከርሱ…
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በሁለት ነገሮች መካከል ምርጫ ሲሰጣቸው ወንጀል እስካልሆነ ድረስ የሚመርጡት ገሩን ነው። ወንጀል ከሆነ ግን ከርሱ እጅግ የሚርቁ ነበሩ።
የአማኞች እናት ከሆነችው ከዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በሁለት ነገሮች መካከል ምርጫ ሲሰጣቸው ወንጀል እስካልሆነ ድረስ የሚመርጡት ገሩን ነው። ወንጀል ከሆነ ግን ከርሱ እጅግ የሚርቁ ነበሩ። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የአላህ ክልከላ ስትደፈር ካልሆነ በቀር ለነፍሳቸው ተበቅለው አያውቁም። የአላህ ክልከላ ስትደፈር ግን ለአላህ ብለው ይበቀላሉ።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Português සිංහල Русский Kiswahili অসমীয়া Tiếng Việt ગુજરાતી Nederlands മലയാളം Românăالشرح
የአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ስለአንዳንድ የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ስነምግባር ተናገረች። ከጠቀሰቻቸውም መካከል: እርሳቸው በሁለት ነገሮች መካከል ምርጫ ሲሰጣቸው የሚመርጡት ገሩን ነው። ግን ያ ገር ነገር ወንጀል እስካልሆነ ድረስ ነው። ገር ነገሩ ወንጀል ከሆነ ግን ከሰዎች ሁሉ እጅግ የሚርቁት እርሳቸው ናቸው። ጠንከር ያለውንም ይመርጣሉ። ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለነፍሳቸው ብቻ ብለው አልተበቀሉም። ይልቁንም የአላህ ክልከላ እስካልተደፈረ ድረስ ስለነፍሳቸው ሐቅ ይቅር የሚሉና የሚያልፉ ነበሩ። ለአላህ ብለው ግን ይበቀሉ ነበር። እጅግ በጣም ለአላህ ብለው የሚቆጡ ነበሩ።فوائد الحديث
ወንጀል እስካልሆነ ድረስ በነገሮች ላይ ቀላሉን መውሰድ እንደሚወደድ እንረዳለን።
የእስልምናን ገርነት እንረዳለን።
ለአላህ ብሎ መቆጣት በሸሪዓ የተደነገገ እንደሆነ እንረዳለን።
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የነበሩበት የቻይነት፣ የትዕግስት፣ የአላህን ህግ በአግባቡ በመፈፀም ላይ የመቆም ማንነታቸውን እንረዳለን።
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ከባድ ነገርን ከመምረጥ መተው፣ በቀላሉ መብቃቃትና የግድ ባልሆነ ነገር ላይ ችክ ማለትን መተው እንደሚገባ ያስረዳናል።"
በአላህ ሐቅ ላይ እስካልሆነ ድረስ ይቅር በማለት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።