አዋጅ! በርግጥ አስካሪ መጠጥ ክልክል ተደርጓል።

አዋጅ! በርግጥ አስካሪ መጠጥ ክልክል ተደርጓል።

ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «በአቡ ጦልሓ ቤት ውስጥ ለሰዎች መጠጥ እየቀዳሁ የማጠጣው እኔ ነበርኩ። የዛን ግዜ ይጠጡት የነበረው አስካሪ መጠጥ በተምር የሚሰራ ነበር። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ተብሎ አዋጅ እንዲነገር አዘዙ: "አዋጅ! በርግጥ አስካሪ መጠጥ ክልክል ተደርጓል።" አቡ ጦልሓ ለኔ እንዲህ አለኝ: "ውጣና ድፋው" እኔም ወጥቼ ደፋሁት በመዲናም መንገድ ፈሰሰ። አንዳንድ ሰዎችም "ሰዎች አስካሪ መጠጥ በሆዳቸው እያለ አለቀላቸዋ!" አሉ። እነርሱን በማስመልከትም አላህ ይህንን አወረደ: {በእነዚያ ባመኑትና በጎ ስራዎችን በሰሩት ላይ (ከመከልከሉ በፊት) በተመገቡት ነገር ኀጢአት የለባቸውም።… } [አልማኢዳህ: 93]»

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

አነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) የእናቱ ባል በነበረው በአቡ ጦልሓ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - ቤት ውስጥ ለሚመጡ ሰዎች መጠጥ የሚቀዳው እርሱ እንደነበር ተናገረ። የዛን ግዜ አስካሪ መጠጥ የሚያዘጋጁትም "ቡስር" (ቢጫው ያልበሰለ) ተምር እና ከበሰለው ተምር ቀላቅለው ነበር። ድንገት በአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ትእዛዝ "አዋጅ! በርግጥም አስካሪ መጠጥ ክልክል ተደርጓል።" ተብሎ አዋጅ ተነገረ። አቡ ጦልሓም ለኔ እንዲህ አለኝ "ውጣና ድፋው አፍስሰው!" እኔም ወጥቼ ደፋሁት አፈሰስኩት። አስካሪ መጠጡም በመዲና መንገድ መፍሰሱን ቀጠለ። አንዳንድ ሰዎችም እንዲህ አሉ: "አንዳንድ ሶሐቦች አስካሪ መጠጥ ክልክል ከመደረጉ በፊት ሆዳቸው ውስጥ እያለ ተገድለዋል!" አላህም እነርሱን በማስመልከት ይህንን አወረደ: {በእነዚያ ባመኑትና በጎ ስራዎችን በሰሩት ላይ (ከመከልከሉ በፊት) በተመገቡት ነገር ኀጢአት የለባቸውም።… } [አልማኢዳህ: 93] ማለትም: በነዚያ ባመኑት ላይ አስካሪ መጠጥ ክልክል ከመደረጉ በፊት በበሉትና በጠጡት ምክንያት ወንጀል የለባቸውም ማለት ነው።

فوائد الحديث

አቡ ጦልሓና ሶሐቦች (ረዲየሏሁ ዐንሁም) በፍጥነት ምንም ማብራሪያ ሳይጠይቁ የአላህን ትእዛዝ መቀበላቸው የነርሱን ደረጃ ያስረዳናል። ይህንንም ነው አንድ ትክክለኛ ሙስሊም ሊያደርግ የሚገባው።

ኸምር: ለሁሉም አስካሪ መጠጥ የሚውል የወል ስም ነው።

ፈዲኽ: ማለት ከ"ቡስር" (ቢጫው ያልበሰለ) ተምር እና ከበሰለ ተምር ተቀላቅሎ እሳት ሳይነካው የሚዘጋጅ አስካሪ መጠጥ ነው።

ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: «ሙሀለብ እንዲህ ብለዋል: "ኸምር መንገድ ላይ የተደፋበት ምክንያት መተዉን ለማወጅና መከልከሉ እንዲታወቅ ነው። ይህም መንገድ ላይ በመድፋት ከሚመጣው ጉዳት ይልቅ የሚያመጣው ጥቅም የጎላ ስለሆነ ነው።"»

አላህ ለባሮቹ ያለው እዝነት መገለፁ፤ ይህም ህግን ከማውረዱ በፊት በድርጊት አለመተሳሰቡ ነው።

አላህ አስካሪ መጠጥን ክልክል አድርጓል። ይህም አስካሪ መጠጥ አይምሮንም ገንዘብንም የሚጎዳ ብክለት ስለሚያስከትል ነው። በአስካሪ መጠጥ ምክንያት የሰው ልጅ አይምሮው ስለሚወገድ በርካታ ወንጀሎችን ይፈፅማል።

التصنيفات

የቁርአን አንቀጾች መውረድ ምክንያት, የተከለከሉ መጠጦች