إعدادات العرض
የከለከልኳችሁን ነገር ራቁ፤ ካዘዝኳችሁም ነገር የቻላችሁትን ያህል ፈፅሙ!
የከለከልኳችሁን ነገር ራቁ፤ ካዘዝኳችሁም ነገር የቻላችሁትን ያህል ፈፅሙ!
ከአቡ ሁረይራ ዐብዱራሕማን ቢን ሶኽር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: "የከለከልኳችሁን ነገር ራቁ፤ ካዘዝኳችሁም ነገር የቻላችሁትን ያህል ፈፅሙ! ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች ያጠፋቸው ጥያቄ ማብዛታቸውና ነቢያቶቻቸውን መቃረናቸው ነው።"»
الترجمة
العربية Español English اردو Indonesia বাংলা Français Türkçe Русский Bosanski සිංහල हिन्दी 中文 فارسی Tiếng Việt Tagalog Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் ไทย Deutsch پښتو অসমীয়া Shqip Nederlands ગુજરાતી Кыргызча नेपाली Lietuvių دری Српски тоҷикӣ Kinyarwanda Română Magyar Čeština Moore Malagasy Oromoo ಕನ್ನಡ Wolof Azərbaycan O‘zbek Українська ქართული Македонски ភាសាខ្មែរ ਪੰਜਾਬੀ मराठी Kirundi Kurmancî Bahasa Melayuالشرح
የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አንድ ነገር የከለከሉን ጊዜ ያለምንም መለየት ሁሉንም ክልከላዎች መራቅ በኛ ላይ ግዴታ እንደሆነና አንድ ነገር ያዘዙን ጊዜ ደግሞ የምንችለውን ያህል መስራት በኛ ላይ ግዴታ እንደሆነ ገለፁልን። ቀጥለውም እንደአንዳንድ የቀደሙ ህዝቦች አይነት አጠፋፍ እንዳንጠፋ አስጠነቀቁን። እነዚህ የቀደሙ ህዝቦች ነቢያቶቻቸውን በመቃረናቸውምና ጥያቄዎችን በማብዛታቸው አላህ በጥፋትና ውድመት አይነት ቀጣቸው። ስለዚህ እነርሱ እንደጠፉት እንዳንጠፋ እነደነርሱ ከመሆን መራቅ ይገባናል።فوائد الحديث
ይህ ሐዲሥ ትእዛዝን መፈፀምና ክልከላን መራቅ ግዴታ መሆኑን በማብራራቱ ረገድ መርህ የሆነ ሐዲሥ ነው።
ክልከላን ለመዳፈር ምንም የተግራራ መንገድ የለም። ትእዛዝን ለመፈፀም ግን በመቻል ገደብ ተገደበ። ይህም የሆነው መተው የሚጠይቀው አቅም ስለሌለና መስራት ግን የታዘዙትን ድርጊት ለማስገኘት የሚጠይቀው አቅም ስላለ ነው።
ጥያቄን ማብዛት መከልከሉን እንረዳለን። ዑለማዎች መጠየቅን ለሁለት ከፍለውታል: አንደኛው: የሚያስፈልገውን ሃይማኖታዊ ጉዳይ በመማር መልኩ መጠየቅ ነው። በዚህ አላማ መጠየቅ ታዟል። የሶሐቦችም ጥያቄ በዚህ መልኩ ነበር። ሁለተኛው: ጥያቄን ለመፍጠር በመጨነቅና በግትርነት መልኩ መጠየቅ ሲሆን ይህኛው ግን የተከለከለው የመጠየቅ አይነት ነው።
ይህ ኡማ ከዚህ በፊት የነበሩት ህዝቦች ነቢያቸውን እንደተቃረኑት ነቢያቸውን ከመቃረን መከልከላቸውን እንረዳለን።
ክልከላን መራቅ ትንሹንም ብዙውንም ያካተተ ነው። ምክንያቱም ሐራምን መራቅ የሚገኘው ትንሹንም ብዙውንም በመራቅ ብቻ ነውና። ለምሳሌ መልክተኛው ከአራጣ ከለከሉን። ይህ ክልከላ ትንሹንም ብዙውንም አራጣ ያካትታል።
ወደ ሐራም የሚያደርሱ ምክንያቶችን መተው እንደሚገባ እንረዳለን። ምክንያቱም መራቅ የሚለው ትርጓሜ ከነመዳረሻዎቹ መራቅን የሚያጠቃልል ነውና።
አንድ ሰው የመልክተኛውን -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ትእዛዝ በሰማ ጊዜ ግዴታ ነው ወይስ ተወዳጅ ነው ብሎ መጠየቅ አይገባውም። ይልቁንም ለመተግበር ነው መቻኮል ያለበት። ይህም "የቻላቹትን ያህል ፈፅሙ!" ከሚለው የምነወስደው ትምህርት ነው።
ጥያቄ ማብዛት በተለይ የሩቅ ጉዳዮችን፣ የትንሳኤ ቀንን የሚመለከት አይነቱ መልሱ ሊደረስበት የማይችል ጉዳይ ላይ አብዝቶ መጠየቅ የጥፋት ምክንያት ነው። ይህን በመሰሉ ጉዳዮች ጥያቄ አታብዛ ትጠፋለህም፤ ወሰን የሚያልፍም ትሆናለህ።
