ምላስህ አላህን በማውሳት ከመርጠብ አይወገድ።

ምላስህ አላህን በማውሳት ከመርጠብ አይወገድ።

ከዐብደላህ ቢን ቡስር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ በመምጣት እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የእስልምና ድንጋጌዎች በርግጥም በኛ ላይ በዙብን። አጥብቄ የምይዘውን ዋናውን በር ይንገሩን።" እርሳቸውም እንዲህ አሉ: "ምላስህ አላህን በማውሳት ከመርጠብ አይወገድ።"» በሌላ ዘገባ: በሙዓዝ ቢን ጀበል - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ሐዲሥ እንደተላለፈው: ሙዓዝ እንዲህ አሉ: «"የአላህን መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የተለያየሁት የመጨረሻ ንግግሬ "ወደ አላህ እጅግ የሚያቃርበኝና መልካሙ ስራ ማንኛው ስራ ነው?" የሚል ነበር። እርሳቸውም: "ምላስህ አላህን ዓዘ ወጀል በማውሳት እርጥብ ሆኖ መሞትህ ነው።" በማለት መለሱልኝ።»

[ሶሒሕ ነው።] [رواه أحمد والترمذي وابن ماجه وابن حبان]

الشرح

አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከደካማነቱ አንፃር ግዴታ ያልሆኑ አምልኮዎች እስኪያቅቱት ድረስ መብዛታቸው እንደተሰማው ስሞታ አቀረበ። ቀጥሎም ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ብዙ ምንዳ የሚያመጣለት የሆነን አጥብቆ የሚይዘውን ቀላል ስራ እንዲጠቁሙት ጠየቀ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሁሉም ሁኔታና ወቅት ምላሱ በ"ተስቢሕ" (ሱብሐነሏህ)፣ በ"ተሕሚድ" (አልሐምዱሊላህ)፣ ምህረት በመጠየቅ (አስተጝፊሩሏህ)፣ ዱዓ በማድረግና በመሳሰሉት አላህን በማውሳት ዘውትሮ ምላሱን ማንቀሳቀስና ማርጠብ እንዳለበት ጠቆሙት።

فوائد الحديث

አላህን በማውሳት ላይ መዘውተር ያለውን ትሩፋት እንረዳለን።

ከአላህ ችሮታ መካከል ትልቁ ምንዳን ማግኛ መንገዶችን ማቅለሉ ተጠቃሽ ነው።

ባሮች በበጎና መልካም እጣ ፈንታቸው እንደሚበላለጡ እንረዳለን።

እንደ "ሱብሐነላህ"፣ "አልሐምዱሊላህ"፣ "ላኢላሃ ኢለላህ"፣ "አላሁ አክበር"ና ከዚህም ውጪ ያሉ አዝካሮችን ከቀልብ ጋር በማስተሳሰር በምላስ አላህን አብዝቶ ማውሳት የብዙ ግዴታ ያልሆኑ (ሱና) አምልኮዎችን ደረጃ ይይዛል።

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለሁሉም ጠያቂዎች የሚስማማቸውን መልስ እየጠበቁ መመለሳቸውን እንረዳለን።