ሱጁድ በወረድክ ጊዜ መዳፎችህን መሬት ላይ አኑር! ክንድህንም ከፍ አድርግ!

ሱጁድ በወረድክ ጊዜ መዳፎችህን መሬት ላይ አኑር! ክንድህንም ከፍ አድርግ!

ከበራእ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ሱጁድ በወረድክ ጊዜ መዳፎችህን መሬት ላይ አኑር! ክንድህንም ከፍ አድርግ!"»

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶላት ውስጥ ሱጁድ ሲወረድ እጆች እንዴት መሆን እንዳለባቸው ገለፁ። ይህም መዳፎቹን መሬት ላይ ማመቻቸትና ጣቶቹ የተጣበቁ ሆነው ወደ ቂብላ አቅጣጫ ማዞር፤ መዳፎቹንም መሬትን ከማስነካትም ከጎኖቹም አራርቆ በማንሳት ነው።

فوائد الحديث

ሰጋጅ የሆነ ሰው ማድረግ ካለበት ግዴታዎች መካከል መዳፎቹን መሬት ላይ ማኖር ነው። መዳፎች ከሰባቱ የሱጁድ አካላቶች መካከል ሁለቱ ናቸው።

ሁለት ክንዶችን ከመሬት ከፍ ማድረግ እንደሚወደድና አውሬ ክንዶቹን እንደሚያነጥፈው እነርሱን ማንጠፍ እንደሚጠላ እንረዳለን።

አምልኮ ላይ ንቃትን፣ ብርታትንና ፍላጎትን ግልፅ ማድረግ የተደነገገ ነው።

አንድ ሰጋጅ በሁሉም የሱጁድ አካላቶቹ የተደገፈ ጊዜ ሁሉም አካል የሚፈለግበትን የአምልኮ ሐቁን ያገኛል።

التصنيفات

የሶላት አሰጋገድ