إعدادات العرض
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሁለቱ ሱጁዶች መካከል "አላሁመግፊር ሊ ወርሐምኒ ወዓፊኒ ወህዲኒ ወርዙቅኒ" (አላህ ሆይ! ማረኝ፣ እዘንልኝም፣ ጤናን ለግሰኝም፣ ምራኝም፣ ሲሳይን…
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሁለቱ ሱጁዶች መካከል "አላሁመግፊር ሊ ወርሐምኒ ወዓፊኒ ወህዲኒ ወርዙቅኒ" (አላህ ሆይ! ማረኝ፣ እዘንልኝም፣ ጤናን ለግሰኝም፣ ምራኝም፣ ሲሳይን ለግሰኝም) ይሉ ነበር።
ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሁለቱ ሱጁዶች መካከል "አላሁመግፊር ሊ ወርሐምኒ ወዓፊኒ ወህዲኒ ወርዙቅኒ" (አላህ ሆይ! ማረኝ፣ እዘንልኝም፣ ጤናን ለግሰኝም፣ ምራኝም፣ ሲሳይን ለግሰኝም) ይሉ ነበር።
[በማመሳከሪያዎቹ ሐሰን ነው።] [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் සිංහල မြန်မာ ไทย Русский 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands ئۇيغۇرچە دری Magyar Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių Malagasy Kinyarwanda नेपाली Română Српски Soomaali Moore Deutsch Українська Български Wolof Azərbaycan ქართული тоҷикӣ bm Македонскиالشرح
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሶላታቸው ውስጥ በሁለቱ ሱጁዶች መካከል ሙስሊም የሆነ ሰው በእጅጉ የሚፈልጋቸው ጉዳዮችንና የዱንያንም ሆነ የአኺራን መልካም የሰበሰቡ የሆኑትን: ምህረትን፤ የወንጀል መሸሸግን፤ ይቅር መባልን መፈለግ፤ እዝነቱ እንዲያዳርሰው መፈለግ ፤ ከሚያምታታ፣ ዝንባሌው ከሚገፋፋውና ከበሽታዎችም ጤናማ መሆንን መፈለግ ፤ አላህን ለእውነትና በርሱ ላይ በመፅናት ላይ እንዲመራው መጠየቅ፤ የኢማን፣ የእውቀት ፣ የመልካም ስራ፣ ምርጥና ሐላል የገንዘብ ሲሳይ እንዲለግሰው መለመንን ሁሉ ያጠቃለሉ የሆኑትን እነዚህ አምስት ዱዓዎችን ይለምኑ ነበር።فوائد الحديث
በሁለቱ ሱጁዶች መካከል በምንቀመጥ ወቅት ይህ ዱዓእ መደንገጉን እንረዳለን።
ይህ ዱዓእ የዱንያንም ሆነ የአኺራን መልካም ነገሮች ስለጠቀለለ የዚህ ዱዓን ትሩፋትንም እንረዳለን።