የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ሰውዬ ከሰልፍ ኋላ ብቻውን ሲሰግድ ተመለከቱትና ሶላቱን እንዲደግመው አዘዙት።

የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ሰውዬ ከሰልፍ ኋላ ብቻውን ሲሰግድ ተመለከቱትና ሶላቱን እንዲደግመው አዘዙት።

ከዋቢሰህ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: "የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ሰውዬ ከሰልፍ ኋላ ብቻውን ሲሰግድ ተመለከቱትና ሶላቱን እንዲደግመው አዘዙት።"

[ሐሰን ነው።] [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ሰውዬ ለብቻው ከሰልፍ ኋላ ተመለከቱትና ሶላቱን በዚህ ሁኔታ መሰገዱ ትክክለኛነቷን ስለሚያጠፋ ሶላቱን እንዲደግመው አዘዙት።

فوائد الحديث

የህብረት ሶላት ለመስገድ በጊዜ መስጂድ በመግባትና ወደፊት ቀደም በማለት መነሳሳቱን እንረዳለን። ሶላቱ ለመበላሸት እንዳትጋለጥም ከሰልፍ ኋላ ለብቻው አለመስገድንም ያነሳሳል።

ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: «ሶላትን ከሰልፍ ኋላ ለብቻው ከጀመረ በኃላ ከሩኩዕ ከመነሳቱ በፊት ወደ ሰልፍ የገባ ሰው በአቢ በክራህ ሐዲሥ ውስጥ እንደመጣው የመድገም ግዴታ የለበትም። ያለበለዚያ ግን የዋቢሰህ ሐዲሥ ጥቅል ሀሳብ እንደሚያስረዳን የመድገም ግዴታ ይጠበቅበት ነበር።»

التصنيفات

የኢማምና የተከታይ ህግጋት