إعدادات العرض
እኔ የማትጎዳና የማትጠቅም ድንጋይ መሆንህን አውቃለሁ። እኔ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሲስሙህ ባላይህ ኖሮ አልስምህም ነበር።
እኔ የማትጎዳና የማትጠቅም ድንጋይ መሆንህን አውቃለሁ። እኔ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሲስሙህ ባላይህ ኖሮ አልስምህም ነበር።
ከዑመር (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና - እንደተላለፈው: "ዑመር ወደ ጥቁሩ ድንጋይ (ሐጀሩል አስወድ) መጣና ሳመው። እንዲህም አለ: እኔ የማትጎዳና የማትጠቅም ድንጋይ መሆንህን አውቃለሁ። እኔ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሲስሙህ ባላይህ ኖሮ አልስምህም ነበር።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Français Tiếng Việt සිංහල Português Kurdî Русский অসমীয়া Kiswahili Nederlands Hausa ગુજરાતી ไทยالشرح
የአማኞች መሪ ዑመር ቢን ኸጧብ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና - በካዕባ ማእዘን ወደሚገኘው ጥቁር ድንጋይ መጣና ሳመው። እንዲህም አለ "እኔ የማትጎዳና የማትጠቅም ድንጋይ መሆንህን አውቃለሁ። እኔ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሲስሙህ ባላይህ ኖሮ አልስምህም ነበር።"فوائد الحديث
ጦዋፍ የሚያደርጉ ሰዎች በሐጀረል አስወድ (በጥቁሩ ድንጋይ) በኩል ሲያልፉ በቀላሉ ለመሳም ከቻሉ መሳማቸው የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን።
ጥቁሩን ድንጋይ በመሳም የሚፈለገው የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መከተል ነው።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ሀሳቡም ይህ ድንጋይ መጥቀምም ሆነ መጉዳትን አይችልም ነው። እንደማንኛውም እንደማይጎዱና እንደማይጠቅሙ ፍጡራን እርሱም የተፈጠረ ድንጋይ ነው። ዑመር ይህንን ንግግር በዚህ መድረክ ያሰራጨውም በሁሉም ሀገር ምስክር እንዲሆንና ከተለያዩ ሀገራት የተገኙ የሐጅ ሰዎች እንዲሸመድዱት ነው።"
አምልኮ የተገደበ ነው። አላህና መልክተኛው ከደነገጉት ውጪ አይደነገግም።
ጥበቡ ባይታወቅ እንኳ አምልኮዋ ትክክለኛ ከሆነች ትሰራለች። ሰዎች ትእዛዙን ተግባራዊ ማድረጋቸውና መታዘዛቸው ራሱ ከአምልኮ ዋነኛ ጥበቦች መካከል አንዱ ነውና።
እንደ ድንጋይና ከርሱ ውጪ ያሉ መሰል ነገሮችን በሸሪዓ እስካልታዘዘ ድረስ በአምልኳዊ መንገድ እነርሱን መሳም መከልከሉን እንረዳለን።