ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መታጠቢያ ውሃ አቀረብኩኝና በልብስም ሸፈንኩላቸው። እርሳቸውም በእጃቸው ላይ አፈሰሱና ሁለት እጃቸውን አጠቡ። ቀጥለው በቀኝ…

ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መታጠቢያ ውሃ አቀረብኩኝና በልብስም ሸፈንኩላቸው። እርሳቸውም በእጃቸው ላይ አፈሰሱና ሁለት እጃቸውን አጠቡ። ቀጥለው በቀኝ እጃቸው ግራ እጃቸው ላይ እያፈሰሱ ብልታቸውን አጠቡ። በእጃቸውም መሬቱን መቱና ጠረጉት። ቀጥለውም አጠቡት። ተጉመጠመጡ፣ አፍንጫቸው ውስጥም ውሃ አስገቡና አወጡ፣ ፊታቸውንና ክንዳቸውንም አጠቡ። ቀጥለው ጭንቅላታቸው ላይ ውሃ አፈሰሱ፣ በሰውነታቸው ላይም ውሃ አንቧቡ። ቀጥለው ገላቸውን ከታጠቡበት ስፍራ ራቅ አሉና እግራቸውን አጠቡ። ልብስ አቀበልኳቸው እርሳቸው ግን አልፈለጉትም። የሰውነታቸውን ርጥበት በእጃቸው እያራገፉት ሄዱ።

የአማኞች እናት ከሆነችው ከመይሙና (ረዲየላሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መታጠቢያ ውሃ አቀረብኩኝና በልብስም ሸፈንኩላቸው። እርሳቸውም በእጃቸው ላይ አፈሰሱና ሁለት እጃቸውን አጠቡ። ቀጥለው በቀኝ እጃቸው ግራ እጃቸው ላይ እያፈሰሱ ብልታቸውን አጠቡ። በእጃቸውም መሬቱን መቱና ጠረጉት። ቀጥለውም አጠቡት። ተጉመጠመጡ፣ አፍንጫቸው ውስጥም ውሃ አስገቡና አወጡ፣ ፊታቸውንና ክንዳቸውንም አጠቡ። ቀጥለው ጭንቅላታቸው ላይ ውሃ አፈሰሱ፣ በሰውነታቸው ላይም ውሃ አንቧቡ። ቀጥለው ገላቸውን ከታጠቡበት ስፍራ ራቅ አሉና እግራቸውን አጠቡ። ልብስ አቀበልኳቸው እርሳቸው ግን አልፈለጉትም። የሰውነታቸውን ርጥበት በእጃቸው እያራገፉት ሄዱ።

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

የአማኞች እናት መይሙና (ረዲየላሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ስለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የጀናባ ትጥበት ሁኔታ ተናገረች። በቅድሚያ የሚታጠቡበትን ውሃ አቀረበችላቸው። በመሸፈኛም ሸፈነችላቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሚከተሉትን ፈፀሙ: በመጀመሪያ: ውኃ በእጃቸው ላይ አፈሰሱ፤ እቃ ውስጥ ከመክተታቸው በፊትም አጠቧቸው። ሁለተኛ: ውኃ ከቀኝ እጃቸው ግራቸው ላይ አፈሰሱና ከጀናባው ቅሪት የተለጣጠፈውን ለማፅዳት ብልታቸውን አጠቡ። ሶስተኛ: በእጃቸው መሬቱን መቱና ጠረጉት። ቀጥለው ከእጃቸው ላይ ቆሻሻውን ለማስወገድ አጠቡት። አራተኛ: ተጉመጠመጡ: ይህም ውሃን አፋቸው ውስጥ በመክተት አንቀሳቀሱና አሽከርክረው ቀጥሎ ተፉት። "ኢስቲንሻቅም" አደረጉ: ይህም ውሃን አፍንጫቸው ውስጥ በትንፋሻቸው ከሳቡ በኋላ ቀጥሎ ውሃውን አስወጡት። አምስተኛ: ፊታቸውንና ክንዳቸውን አጠቡ። ስድስተኛ: ውሃን በጭንቅላታቸው ላይ አንቧቡ። ሰባተኛ: በተቀረው አካላታቸው ላይም ውሃዉን አንቧቡ። ስምንተኛ: ከታጠቡበት ስፍራ ዘወር ብለው በሌላ ስፍራ መጀመሪያ ያልታጠቡትን እግራቸውን አጠቡ። ቀጥሎ የሚያደራርቁበትን ጨርቅ አመጣችላቸው። እርሳቸው ግን ሳይቀበሏት ውሃውን በእጃቸው ከሰውነታቸው ላይ መጥረግና ማራገፍ ጀመሩ።

فوائد الحديث

የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባለቤቶች የህይወታቸውን ረቂቅ ዝርዝር ጉዳዮችንም በመግለፅ ኡማውን ለማስተማር ትኩረት መስጠታቸውን እንረዳለን።

ይህ የአስተጣጠብ ሁኔታ የተሟላ የሆነው የጀናባ ትጥበት ሁኔታን በመግለፅ ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመጡት የአስተጣጠብ ሁኔታዎች መካከል አንዱ ነው። የሚያብቃቃ የሆነው የጀናባ ትጥበት ደሞ ከመጉመጥመጥና አፍንጫ ውስጥ ውሃ ከመክተት ጋር ሰውነቱን ባጠቃላይ በውሃ ማዳረስ ነው።

ከታጠቡ ወይም ከዉዱእ በኋላ ሰውነትን በጨርቅ ማደራረቅም ይሁን ማደራረቅን መተው ይፈቀዳል።

التصنيفات

ትጥበት