إعدادات العرض
መዚይ (ስሜት በሚቀሰቀስ ወቅት የሚወጣ ፈሳሽ ነው።) የሚበዛብኝ ሰው ነበርኩ። ልጃቸው እኔ ዘንድ በመሆኗ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) (ስለብይኑ) መጠየቅ…
መዚይ (ስሜት በሚቀሰቀስ ወቅት የሚወጣ ፈሳሽ ነው።) የሚበዛብኝ ሰው ነበርኩ። ልጃቸው እኔ ዘንድ በመሆኗ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) (ስለብይኑ) መጠየቅ አፈርኩና ሚቅዳድ ቢን አስወድን እንዲጠይቃቸው አዘዝኩት፤ ጠየቃቸው። እርሳቸውም 'ብልቱን ይታጠብና ዉዱእ ያድርግ።
ከዐሊ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "መዚይ (ስሜት በሚቀሰቀስ ወቅት የሚወጣ ፈሳሽ ነው።) የሚበዛብኝ ሰው ነበርኩ። ልጃቸው እኔ ዘንድ በመሆኗ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) (ስለብይኑ) መጠየቅ አፈርኩና ሚቅዳድ ቢን አስወድን እንዲጠይቃቸው አዘዝኩት፤ ጠየቃቸው። እርሳቸውም 'ብልቱን ይታጠብና ዉዱእ ያድርግ።' አሉ።" በቡኻሪ ዘገባ ደሞ "ዉዱእ አድርግ፤ ብልትህንም እጠብ።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî Kiswahili සිංහල Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá ไทย پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or नेपाली Malagasy Kinyarwanda తెలుగు Lietuvių Oromoo Română മലയാളം Nederlands Soomaali Српски Українська Deutsch ಕನ್ನಡ Wolof Moore Shqip ქართული Azərbaycan Magyarالشرح
ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና መዚይ (ነጭ፣ ቀጭን፣ የሚዝለገለግ፣ ስሜት በሚቀሰቀስ ወቅት ወይም ከግንኙነት በፊት የሚወጣ ፈሳሽ ነው።) ብዙ ጊዜ ይወጣቸው እንደነበር ተናገሩ። መውጣቱን ተከትሎ እንዴት ማድረግ እንዳለባቸውም አያውቁም። የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ልጅ ፋጢማ ባለቤት ስለሆኑ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መጠየቅ አፈሩ። ሚቅዳድ ቢን አስወድ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለዚህ ጉዳይ እንዲጠይቅላቸው አድርገው ላኩት። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ብልቱን አጥቦ ዉዱእ ማድረግ እንደሚገባው በመንገር መልስ ሰጡት።فوائد الحديث
አይነ አፋርነቱ በሰው አማካኝነት እንኳ ከማስጠየቅ አለማቀቡ የዐሊይ ቢን አቢጧሊብን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ደረጃ ያስረዳናል።
ፈትዋ ለመጠየቅ ሰው መተካት እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
አንድ ሰው ስለራሱ የሚያሳፍር ነገርንም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ መናገሩ እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
የመዚይን ነጃሳነትና ከሰውነትም ከልብስም ላይ ማጠብ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
የመዚይ መውጣት ዉዱእን ከሚያፈርሱ ነገሮች መካከል አንዱ መሆኑን እንረዳለን።
ብልትንና ሁለቱን ፍሬዎች ማጠብ እንደሚገባ የሚያዝ ሌላ ሐዲሥ ስላለ ብልትንና ሁለቱን ፍሬዎች ማጠብም ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
التصنيفات
ነጃሳን ማስወገድ