إعدادات العرض
ሰዎች ማፍጠርን እስካቻኮሉ ድረስ መልካም ላይ ከመሆን አይወገዱም።
ሰዎች ማፍጠርን እስካቻኮሉ ድረስ መልካም ላይ ከመሆን አይወገዱም።
ከሰህል ቢን ሰዕድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሰዎች ማፍጠርን እስካቻኮሉ ድረስ መልካም ላይ ከመሆን አይወገዱም።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Français ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî සිංහල Русский Tiếng Việt Kiswahili অসমীয়া ગુજરાતી Nederlands ไทย മലയാളം Românăالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሰዎች ፀሐይ መግባቷን ካረጋገጡ በኋላ ከጾም ማፍጠርን እስካቻኮሉ ድረስ መልካም ላይ ከመሆን አይወገዱም ብለው ተናገሩ። ይህም ሱናን በመተግበራቸውና የተወሰነላቸው ገደብ ላይ በመቆማቸው ነው።فوائد الحديث
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: «ይህ ሐዲሥ ፀሐይ መግባቷ ከተረጋገጠ በኋላ በፍጥነት በማፍጠር ላይ ያነሳሳል። ሀሳቡም ኡመቶቼ ይህን ሱና መጠበቅን እስከዘወተሩበት ድረስ ጉዳያቸው የተስተካከለና ስርዓት የያዘ ከመሆን አይወገድም። ያዘገዩት ጊዜ ደግሞ ይህ ለሚወድቁበት ብልሽት ምልክት ይሆናል።»
ሰዎች ሱናን በመከተላቸው ምክንያት በመካከላቸው መልካም ነገር እንደሚቆይና የነገሮች መበላሸት ሱናን ከመለወጥ ጋር ተያይዞ እንደሚመጣ እንረዳለን።
የመጽሐፍ ባለቤቶችና የቢድዓ ሰዎችን መቃረን እንደሚገባ እንረዳለን። እነርሱ አዘግይተው ነው የሚያፈጥሩትና።
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: «ሐዲሡ ምክንያቱንም አብሮ ገልጿል። ሙሀልለብ እንዲህ ብለዋል: "የዚህም ጥበብ ከምሽቱ ክፍል ቀኑ ላይ እንዳይጨመር ነው። እንዲሁም ለጾመኛው የገራና በአምልኮ ላይም የሚያጠነክረው ስለሆነ ነው። የማፍጠሪያ ወቅትም ፀሐይ መግባቷን በማየት ወይም ሁለት ታማኝ ሰዎች በመናገራቸው የሚረጋገጥ እንደሆነ ዑለማዎች ተስማምተዋል። ልክ እንደዚሁ ሚዛን በሚደፋው የዑለማዎች አቋም መሰረት በአንድ ታማኝ ሰው ንግግር ከተረጋገጠም ማፍጠር ይቻላል።»
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ማሳሰቢያ: ረመዷን ውስጥ ሁለተኛውን የፈጅር አዛን ፈጅር ከመውጣቱ (ጎህ ከመቅቀድ) አንድ ሶስተኛ ሰዓት በፊት በማድረግና መጾም ለፈለገ ሰው የመብላትና የመጠጣት ጊዜው እንዳለቀ ለማሳወቅ በሚል ሙግት የተዘጋጀውን የመብራት ምልክት ማጥፋት በዚህ ዘመን ከሚስተዋሉ ውግዝ ከሆኑ ቢድዓዎች መካከል ነው። ይህንንም የፈለሰፉ ሙብተዲዖች አምልኮ ላይ ጥንቃቄ ለማድረግ ነው ብለው ይሞግታሉ። ይህንንም ምልክት የነሱ ሰዎች ካልሆኑ በቀር አይረዱትም። ቀስ በቀስም ይህ ቢድዓቸው ወቅቱ ላይ እርግጠኛ እንድንሆን ነው በሚል ሙግታቸው ሰበብ ፀሐይ ከገባ በኋላ ካልሆነ በቀር አዛን ላለማድረግ እና የማፍጠሪያ ወቅትንም ለማዘግየት የሰሑርንም ወቅት ለማቻኮል ዳረጋቸው። ስለዚህም በነርሱ ውስጥ መልካሙ መነመነ ክፋቱ በረከተ። አላህን እገዛውን እንማፀናለን።"
التصنيفات
የፆም ሱናዎች