إعدادات العرض
ከወሊዩዋ (አሳዳጊዋ) ፈቃድ ውጪ ያገባች ማንኛዋም ሴት ጋባቻዋ ውድቅ ነው። (ንግግራቸውን ሶስት ጊዜ ደጋግሙት) እርሷን ከተገናኘም በመንካቱ ምክንያት መህሯ የራሷ ነው። ወሊዮች…
ከወሊዩዋ (አሳዳጊዋ) ፈቃድ ውጪ ያገባች ማንኛዋም ሴት ጋባቻዋ ውድቅ ነው። (ንግግራቸውን ሶስት ጊዜ ደጋግሙት) እርሷን ከተገናኘም በመንካቱ ምክንያት መህሯ የራሷ ነው። ወሊዮች ከተጨቃጨቁም ወሊይ ለሌለው ሰው የሙስሊሞች መሪ ወሊዩ ነው።
የአማኞች እናት ከሆነችው ከዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ከወሊዩዋ (አሳዳጊዋ) ፈቃድ ውጪ ያገባች ማንኛዋም ሴት ጋባቻዋ ውድቅ ነው። (ንግግራቸውን ሶስት ጊዜ ደጋግሙት) እርሷን ከተገናኘም በመንካቱ ምክንያት መህሯ የራሷ ነው። ወሊዮች ከተጨቃጨቁም ወሊይ ለሌለው ሰው የሙስሊሞች መሪ ወሊዩ ነው።"»
الترجمة
العربية Bosanski English فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو हिन्दी 中文 ئۇيغۇرچە Kurdî Português Nederlands অসমীয়া Tiếng Việt ગુજરાતી Kiswahili پښتو සිංහල Hausa ไทย Tagalogالشرح
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሴት ልጅ ያለ ወሊዮቿ ፍቃድ ራሷን ማጋባቷን ከለከሉ። ጋብቻዋም ውድቅ ነው የሚሆነው። ጋብቻዋ እንዳልተፈፀመ ለመግለፅም ሶስት ጊዜ ደጋገሙት። ያለ ወሊዩዋ ፈቃድ አግብቷት የተገናኛትም በመገናኘቱ ምክንያት ለርሷ ሙሉ መህር ይሰጣታል። በመቀጠል የወሊዮች ደረጃ እኩል ሆኖ ጋብቻን በማሰሩ ዙሪያ ወሊዮች ከተጨቃጨቁ ጋብቻውን የሚያስረው የቀደመው ነው። ይህም ጥሩ ነገር አይቶላት ከሆነ ነው። ወሊዩዋ ከማጋባት ከታቀበ ወሊይ እንደሌላት ትቆጠራለች። መሪው ወይም ዳኛው ወይም የመሳሰሉት ወሊዩዋ ይሆናሉ። ያለበለዚያ ወሊይ እያለ መሪ ወሊይነት የለውም።فوائد الحديث
ጋብቻ ትክክለኛ እንዲሆን ወሊይ መስፈርት መሆኑን እንረዳለን። ከኢብኑ ሙንዚር ከሶሐቦች መካከል ከአንዱም ከዚህ ተቃራኒ የሆነ አቋም አይታወቅም የሚል ንግግር መጥቷል።
የተበላሸ ጋብቻ ላይ እንኳ ሴቷ ወንዱ እርሷን በመገናኘቱ ልውጫ መህር ይገባታል።
ከነጭራሹ ወሊይ ስለሌላትም ይሁን ወይም ወሊዩ ከማጋባት በመታቀቡም ይሁን ወሊይ ለሌላት ሴት መሪ የርሷ ወሊይ ነው።
ወሊይ በመታጣቱ ወይም በሌላ ችግር ምክንያት ወሊይ ለሌላት ሴት መሪ ወሊይ ተደርጎ ይወሰዳል። በዚህ ጉዳይ ላይ ዳኛውም የመሪውን ቦታ ስለሚተካ ዳኛው የወሊይነትን ቦታም ይተካል።
ሴትን በማጋባት ወሊይ መሆን ማለት እርሷ ሐቅ የላትም ማለት አይደለም። ይልቁንም ለርሷም ሐቅ አላት። ወሊዩዋ ከፍቃዷ ውጪ ሊያጋባትም አይፈቀድለትም።
የትክክለኛ ጋብቻ መስፈርቶች: አንደኛ: ሁለቱንም ጥንዶች በጥቆማ ወይም ስማቸውን በመጥራት ወይም ማንነታቸውን በመግለፅና በመሳሰሉት ለይቶ መጥራት ነው። ሁለተኛ: ሁለቱም ጥንዶች አንዱ ሌላኛውን ወዶ መቀበል አለበት። ሶስተኛ: ለሴቷ ወሊዩዋ ማሰሩ ነው። አራተኛ: በጋብቻው ውል ላይ ምስክር መኖሩ ነው።
ጋብቻውን የሚያስረው ወሊይ ሊያሟላቸው የሚገቡ መስፈርቶች: አንደኛ: የአይምሮ ጤነኝነት ነው። ሁለተኛ: ወንድ መሆኑ ነው። ሶስተኛ: አስራ አምስት አመት በመድረስ ወይም የዘር ፈሳሽ በመውጣቱ ለአቅመ አዳም መድረሱ ነው። አራተኛ: ሃይማኖታቸው አንድ አይነት መሆኑ ነው። ካፊር የሆነ ሰው ለሙስሊም ወንድም ሆነ ለሙስሊም ሴት ወሊይ የመሆን መብት የለውም። ልክ እንደዚሁ ሙስሊም የሆነ ሰውም ለካፊር ወንድም ይሁን ሴት ወሊይ የመሆን መብት የለውም። አምስተኛ: የአመፀኝነት ተቃራኒ የሆነ ታማኝነት ሊኖረው ይገባል። ለዚህም የጋብቻዋን ጉዳይ ሃላፊነት ለወሰደላት ልጅ ጥቅም ትኩረት ማድረግ መቻሉ ራሱ በቂ ነው። ስድስተኛ: ወሊዩ ቂል ያልሆነ ቀና ሰው መሆኑ ነው። ይህም ለልጅቷ ቢጤዋንና የጋብቻን ጥቅሞች ማወቅ የሚችል መሆኑ ነው።
በማጋባት ጉዳይ ለሴት ወሊይ እንዲሆን ፉቀሃኦች ያስቀመጡት ቅደም ተከተል አለ። ቅርብ የሆነ ወሊይ የጠፋ ወይም መስፈርቶቹን ያላሟላ ጊዜ ካልሆነ በቀር እርሱን መተላለፍ አይፈቀድም። የሴት ልጅ ወሊይ አባቷ ነው። ቀጥሎ አባቷ የተናዘዘለት ነው። ቀጥሎ በአባቷ በኩል ያለው አያቷ ነው። ከዛም ከፍ ቢል እንደዛው። ቀጥሎ ልጇ ነው። ቀጥሎ የልጅ ልጆቿ ናቸው። ከዛም ዝቅ ቢሉ እንደዛው። ከዛም የአባትና የእናቷ ልጅ የሆነ ወንድሟ ነው። ከዚያም በአባት ብቻ የምትዛመደው ወንድሟ ነው። ከዚያም የነዚህ (ወንድሞቿ) ልጆች ናቸው። ከዚያም የአባቷ ወንድም (በአባትም በእናትም አንድ የሆኑ) አጎቷ ነው። ከዚያም የአባቷ ወንድም (በአባት ብቻ አንድ የሆኑ) አጎቷ ነው። ከዚያም በአባቷ በኩል ያሉ የአጎቶቹቿ ልጆች ናቸው። ከዚያም ልክ እንደ ውርስ በዘር (ዝምድና) ወራሽ የሆኑት በጣም ቅርብ ዘመዶቿ በቅርበታቸው ልክ ናቸው። ወሊይ ለሌለው ሰው ሙስሊም መሪ እና እሱን ወክሎ የሚሰራ ዳኛ ወሊይ ናቸው።
التصنيفات
ጋብቻ