إعدادات العرض
እጅህን የሚያምህ ሰውነት ላይ አድርግና ሶስት ጊዜ "ቢስሚላህ" በል። ሰባት ጊዜ ደግሞ "አዑዙ ቢላሂ ወቁድረቲሂ ሚንሸሪ ማአጂዱ ወኡሓዚሩ" በል።» አሉት።" ትርጉሙም "ከሚሰማኝ ህመምና…
እጅህን የሚያምህ ሰውነት ላይ አድርግና ሶስት ጊዜ "ቢስሚላህ" በል። ሰባት ጊዜ ደግሞ "አዑዙ ቢላሂ ወቁድረቲሂ ሚንሸሪ ማአጂዱ ወኡሓዚሩ" በል።» አሉት።" ትርጉሙም "ከሚሰማኝ ህመምና ከምፈራው አደጋ ክፋት በአላህና በችሎታው እጠበቃለሁ።" ማለት ነው።
ከዑሥማን ቢን አቢልዓስ አሥሠቀፊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እርሱ ከሰለመ ጊዜ ጀምሮ ሰውነቱ ውስጥ ስለሚሰማው ህመም ለአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አማከረ። የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለርሱ እንዲህ አሉት: «እጅህን የሚያምህ ሰውነት ላይ አድርግና ሶስት ጊዜ "ቢስሚላህ" በል። ሰባት ጊዜ ደግሞ "አዑዙ ቢላሂ ወቁድረቲሂ ሚንሸሪ ማአጂዱ ወኡሓዚሩ" በል።» አሉት።" ትርጉሙም "ከሚሰማኝ ህመምና ከምፈራው አደጋ ክፋት በአላህና በችሎታው እጠበቃለሁ።" ማለት ነው።
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt සිංහල Kurdî Português Nederlands অসমীয়া Kiswahili ગુજરાતી پښتو ไทย Hausa Română മലയാളം Deutsch नेपाली Oromooالشرح
ዑሥማን ቢን አቢልዓስን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ሊገድለው የቀረበ የሆነ በሽታ አጋጥሞት ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሊጠይቁት መጡ። አላህ ያረፈበትን በሽታ እንዲያስወግድለት የሚያደርግ ዱዓንም አስተማሩት። ይሀውም የሚያመው ስፍራ ላይ እጁን በማድረግ ሶስት ጊዜ (ቢስሚላህ) ማለት ቀጥሎም ሰባት ጊዜ ይህንን ማለት (አዑዙ) እጠጋለሁ፣ እጠበቃለሁ (ከሚሰማኝ ክፋት በአላህና በችሎታው) አሁን ላይ ከሚያመኝ ህመም ማለት ነው። (ከምፈራው) ለወደፊት ከሚያገኘኝና ከምፈራው ሀዘንና ፍርሃት ወይም ይህ በሽታ ከመቀጠሉና ህመሙ በሰውነቴ ውስጥ ከመሰራጨቱ በአላህ እጠበቃለሁ ማለት ነው።فوائد الحديث
ሐዲሡ ውስጥ እንደመጣው የሰው ልጅ ራሱ ላይ ሩቃ መቅራቱ እንደሚወደድ እንረዳለን።
ማማረርና መቃወም በሌለበት መልኩ ህመምን ለሌሎች መንገር ከተወኩልና ትእግስት ጋር አይጋጭም።
ዱዓ ሰበቦችን ከመጠቀም መካከል አንዱ ነው። ስለዚህም በተነገሩን ቃላቶቹና በቁጥሮቹ ላይ ብቻ መወሰን ይገባል።
ይህ ዱዓ ለሁሉም የሰውነት ህመም ይሆናል።
ይህን ዱዓ ሩቃ በሚያደርግበት ወቅት እጅን የሚያመው ስፍራ ላይ ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን።
التصنيفات
ሸሪዓዊ ሩቃ