አዛን ሲባል የሰማ ጊዜ: 'አሽሃዱ አን ላኢላሃ ኢለሏሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ ወአነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ ረዲቱ ቢላሂ ረበን ወቢሙሐመደን ረሱለን ወቢል ኢስላሚ ዲና' ያለ ሰው ወንጀሉ…

አዛን ሲባል የሰማ ጊዜ: 'አሽሃዱ አን ላኢላሃ ኢለሏሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ ወአነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ ረዲቱ ቢላሂ ረበን ወቢሙሐመደን ረሱለን ወቢል ኢስላሚ ዲና' ያለ ሰው ወንጀሉ ይማራል።" (ትርጉሙም: ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም። ብቸኛና አጋር የሌለው ነው። ሙሐመድም የአላህ ባሪያውና መልክተኛው ናቸው ብዬ እመሰክራለሁ፤ በአላህ ጌትነት፣ በሙሐመድ መልክተኝነት፣ በኢስላም ሃይማኖትነት ወድጃለሁ።)

ከሰዕድ ቢን አቢ ወቃስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አዛን ሲባል የሰማ ጊዜ: 'አሽሃዱ አን ላኢላሃ ኢለሏሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ ወአነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ ረዲቱ ቢላሂ ረበን ወቢሙሐመደን ረሱለን ወቢል ኢስላሚ ዲና' ያለ ሰው ወንጀሉ ይማራል።" (ትርጉሙም: ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም። ብቸኛና አጋር የሌለው ነው። ሙሐመድም የአላህ ባሪያውና መልክተኛው ናቸው ብዬ እመሰክራለሁ፤ በአላህ ጌትነት፣ በሙሐመድ መልክተኝነት፣ በኢስላም ሃይማኖትነት ወድጃለሁ።)

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: አዛን አድራጊውን የሰማ ጊዜ እንዲህ ያለ ሰው: "አሽሃዱ አን ላኢላሃ ኢለሏሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ" ማለትም: ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለና ከርሱ ውጪ የሚመለኩ ሁሉ ከንቱ እንደሆኑ አረጋግጣለሁ፣ አውቃለሁ፣ እናገራለሁ። "ወአነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ" ማለትም: እርሳቸው ባሪያ ናቸውና አይመለኩም፣ መልክተኛ ናቸውና አይስተባበሉም። "ረዲቱ ቢላሂ ረበን" ማለትም: በአላህ ጌትነት፣ ተመላኪነትና በስሞቹና በባህሪያቱ ወድጃለሁ። ማለት ነው። "ወቢሙሐመደን ረሱላ" ማለትም ረሱል በተላኩበት ነገር ሁሉና ባደረሱን ነገር ወድጃለሁ። ማለት ነው። "በእስልምናም" ማለትም: ትእዛዛትም ሆኑ ክልከላዎች በሁሉም የኢስላም ህግጋት "ዲና" ማለትም በማመንና በመመራት ወድጃለሁ። ማለት ነው። "ወንጀሉ ይማራል።" ማለትም ትናንሽ ወንጀሎቹን ይማሩለታል።

فوائد الحديث

ይህን ዱዓ አዛን በሚሰሙ ጊዜ መደጋገም ወንጀልን ያስምራል።

التصنيفات

አዛንና ኢቃማህ, አዛንና ኢቃማህ