إعدادات العرض
የጀነት ሰዎች ጀነት የገቡ ጊዜ አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ይላል "አንዳች ነገር እንድጨምርላችሁ ትፈልጋላችሁን?
የጀነት ሰዎች ጀነት የገቡ ጊዜ አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ይላል "አንዳች ነገር እንድጨምርላችሁ ትፈልጋላችሁን?
ከሱሀይብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: «የጀነት ሰዎች ጀነት የገቡ ጊዜ አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ይላል "አንዳች ነገር እንድጨምርላችሁ ትፈልጋላችሁን?" እነርሱም "ፊታችንን አላበራህልንምን? ጀነት አስገብተህስ ከእሳት አላዳንከንምን?" ይላሉ። ነቢዩ እንዲህ አሉ "የፊቱን ግርዶሽ ይገልጣል። ወደ ጌታቸው ዐዘ ወጀል ከመመልከት የበለጠ ተወዳጅ የሆነ አንዳችም ነገር አልተሰጣቸውም።"»
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt Hausa Kurdî Português සිංහල Nederlands অসমীয়া Kiswahili ગુજરાતી پښتو ไทย Română മലയാളം Deutsch Oromoo नेपालीالشرح
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የጀነት ሰዎች ጀነት የገቡ ጊዜ አላህ ተባረከ ወተዓላ ለነርሱ እንዲህ እንደሚል ተናገሩ: እንድጨምርላችሁ የምትፈልጉት አንዳች ነገር አለን? ሁሉም የጀነት ሰዎችም እንዲህ ይላሉ: ፊታችንን አላበራኸውምን? ጀነት አስገብተህስ ከእሳት አላዳንከንምን? አላህም ግርዶሹን አስወግዶ ይገልጠዋል። የፊቱ ግርዶሽም ብርሃን ነው። ወደ ጌታቸው ዐዘ ወጀል ከመመልከት የበለጠ ተወዳጅ ነገርም አይሰጣቸውም።فوائد الحديث
የጀነት ሰዎች ግርዶሹ ተገልጦ ጌታቸውን ሲመለከቱ ከሀዲያን ግን ጌታቸውን ከማየት የተነፈጉ ናቸው።
ከጀነት ፀጋዎች ትልቁ ፀጋ አማኞች ጌታቸውን መመልከታቸው ነው።
የጀነት ሰዎች ሁሉ ደረጃቸው የተለያየ ቢሆን እንኳ ጌታቸውን ይመለከታሉ።
አላህ አማኞችን ጀነት በማስገባት ችሮታውን እንደሚውል እንረዳለን።
በመልካም ተግባርና አላህንና መልክተኛውን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በመታዘዝ ወደ ጀነት መቻኮል አንገብጋቢ እንደሆነ እንረዳለን።
التصنيفات
የጀነትና እሳት ባህሪዎች