إعدادات العرض
'አሁን ላይ እኔ ያላየኋቸው ሁለት አይነት የእሳት ባለቤቶች አሉ። (እነሱም) ሰዎችን የሚደበድቡበት እንደከብት ጭራ የመሰለ አለንጋ ያላቸው ሰዎች እና ለብሰው የተራቆቱ የሆኑ ራሳቸው…
'አሁን ላይ እኔ ያላየኋቸው ሁለት አይነት የእሳት ባለቤቶች አሉ። (እነሱም) ሰዎችን የሚደበድቡበት እንደከብት ጭራ የመሰለ አለንጋ ያላቸው ሰዎች እና ለብሰው የተራቆቱ የሆኑ ራሳቸው ተዘንብለው ሌሎችን ለክፉ የሚጋብዙ፤ ጭንቅላታቸው እንደተዘነበለ የግመል ሻኛ የሆነ ሴቶች ናቸው።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: 'አሁን ላይ እኔ ያላየኋቸው ሁለት አይነት የእሳት ባለቤቶች አሉ። (እነሱም) ሰዎችን የሚደበድቡበት እንደከብት ጭራ የመሰለ አለንጋ ያላቸው ሰዎች እና ለብሰው የተራቆቱ የሆኑ ራሳቸው ተዘንብለው ሌሎችን ለክፉ የሚጋብዙ፤ ጭንቅላታቸው እንደተዘነበለ የግመል ሻኛ የሆነ ሴቶች ናቸው። እነዚህ ጀነት አይገቡም፤ መዓዛዋንም አያገኙም። የጀነት ሽታዋም (እነሱ ካሉበት) የሆነ ያክል ርቆ ይገኛል።'"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Português සිංහල Svenska ગુજરાતી Yorùbá Tiếng Việt Kiswahili پښتو অসমীয়া دری Кыргызча Malagasy or Čeština नेपाली Oromoo Română Nederlands Soomaali తెలుగు ไทย Српски മലയാളം Kinyarwanda ಕನ್ನಡ Lietuviųالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁለት አይነት ሰዎች የእሳት ባለቤቶች እንደሆኑና በሳቸው ዘመን እንዳላዩዋቸውና እንደሌሉ፤ በተቃራኒው ከርሳቸው ህልፈት በኋላ እንደሚመጡ ተናገሩ። የመጀመሪያው አይነት ሰዎች: ሰዎችን የሚመቱበት የከብት ጭራ የሚያክል አለንጋ ይዘው የሚዞሩ ሰዎች ናቸው። እነርሱም ሰዎችን ያለ አግባብ በመምታት የግፈኞች ተባባሪ የሆኑ ፖሊሶች ናቸው። ሁለተኛው አይነት ሰዎች ደግሞ: በተለምዶ የሴቶች ተፈጥሮ የሆነውን የጥብቅነትንና አይነ አፋርነትን ልብስ ያወለቁ ሴቶች ናቸው። በተጨባጭ ገላቸው ላይ ልብስ ያለ ቢሆንም በትክክለኛው ግን የተራቆቱ ናቸው። ምክንያቱም እነሱ ቆዳቸውን ግልፅ ለማውጣት ሰውነትን የሚያሳይ ቀጭን ልብስ ነውና የሚለብሱት፤ (ወይ) ውበታቸውን ለማጉላት የተወሰነ ሰውነታቸውን ሸፍነው የተወሰነውን የገለጡ ናቸውና በማለት እነዚህን ሴቶች ገለጿቸው። በአለባበሳቸውና በአረማመዳቸው የወንዶችን ቀልብ ወደነርሱ እንዲያዘነብል የሚያደርጉ፣ ትከሻዎቻቸውንም የሚያወዛውዙ፣ ሌሎችንም እነርሱ ወደ ወደቁበት ጥመት እንዲያዘነብሉ የሚያደርጉ ናቸው። ከነዚህ ሴቶች ባህሪ መካከልም: ጭንቅላታቸው ያዘነበለ የግመል ሻኛ ይመስላል። የፀጉራቸውን መጠን በማሰሪያና በመሳሰሉት በማሰር ያተልቋታል። በግመል ሻኛ የተመሳሰሉት ፀጉራቸውና ጉንጉናቸው ከጭንቅላታቸው በላይ ከፍ ስለሚልና የግመል ሻኛ እንደሚዘነበለው ፀጉራቸውን በሚጎነጎኑት ሳቢያ ወደአንድ ጎን እስኪዘነበል ድረስ ሰበር ስለሚል ነው። ይህን ባህሪ የተላበሱ ሴቶች እነርሱ ላይ ይህ ከባድ ዛቻ አለባቸው። እርሱም ጀነት ላይገቡ፣ ሽታዋንም ላያገኙ፣ ወደርሷም ላይቀርቡ ነው። የጀነት መዓዛ ከሩቅ ስፍራ ነው የሚሸተው።فوائد الحديث
ሰዎችን ወንጀል ሳይሰሩ ወይም ኃጢአት ሳይተገብሩ መምታትና ማወክ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
ግፈኞችን በግፋቸው ላይ ማገዝ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
ሴቶች ከመገላለጥ፣ ከመራቆት፣ ሀፍረተ ገላን ከሚገልፅ ወይም ቅርፅን ከሚያሳይ ጠባብና ስስ ልብስ መጠንቀቅ እንዳለባቸው።
ሙስሊም ሴቶች የአላህን ትእዛዝ አጥብቀው በመያዝ ላይና አላህን ከሚያስቆጣውና በመጨረሻው ዓለም አሳማሚና ዘውታሪ ቅጣት እንዲገባቸው ከሚያደርጓቸው ነገር እንዲርቁ መነሳሳቱን እንረዳለን።
ይህ ሐዲሥ የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ነቢይነት ከሚጠቁሙ ሐዲሦች አንዱ ነው። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) (በህይወት ዘመናቸው) ያልተከሰተ ሩቅ ጉዳይን ተናገሩ እንደተናገሩትም ተከሰተ።
التصنيفات
የጀነትና እሳት ባህሪዎች